በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 09, 2026)

ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ቁጥር

02/2018

በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ልዩ ቦታ ሳሪስ ጤና ጣቢያ አደይ አበባ ሙኒከ ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ ያገለገሉ ከ40 አይነት በላይ እቃዎች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። እቃዎቹ የሚገኝበት ሳሪስ ጤና ጣቢያ ጊቢ ውስጥ ሆኖ የዋጋ መሙያ ሰነድ እና የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 35 ይገኛል። ማንኛውም ተጫራች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከሳሪስ ጤና ጣቢያ ከፋ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ማለትም ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች ሽያጭ 7000.00(ሰባት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ (CPO) በአድራሻችን ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ሰነድ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ከገባ በኋላ እና አሸናፊው ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከውድድሩ ቢወጡ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል። ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸቸው ባሉበት ሳሪስ ጤና ጣቢያ ካርድ ክፍል ፊት ለፊት ባለው አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ሂደት በተቀመጠው መሰረት ይካሄዳል።

የጨረታ መዝጊያ እና መከፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። ተጫራቾች ከመስሪያ ቤቱ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉን በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጅምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ መስሪያ ቤቱ በሚያዘው የክፍያ አማራጭ ገቢ በማድረግ እቃውን ከቦታው ማንሳት ያለበት ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ዋስትና የሚወረስ ይሆናል። ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- እቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 06 ሳሪስ ጤና ጣቢያ 3F ፌት ለፊት ከሙኒክ ሆቴል አጠገብ

ስልክ:-011 470-9869/ 011 470-7977

በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የሳሪስ ጤና ጣቢያ