Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የብረት መደርደሪያ ሼልፍ እና የሻተር አቅርቦት ከነ ስራው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 10, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡ አአትማባ/ብግጨ ግዳ ዕቃ/07/2018
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባልስልጣን ከታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ፦
- ሎት 1 “ የብረት መደርደሪያ ሼልፍ”
- ሎት 2 “የሻተር አቅርቦት ከነ ስራው “
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ፦
1. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በባለስልጣኑ ግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10-01 መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለሚያቀርቡት አገልግሎት ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት 50ሺብር (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው።
5. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በባለስልጣኑ ግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዋና ክፍል በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም በማስያዝ እና ውል መፈረም አለባቸው፣
6. የጨረታው አሸናፊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፣
7. ጨረታው የካቲት 20/2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ይዘጋል፣
8. ጨረታው የካቲት 20/2018 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
9. ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
10. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ሃያ ሁለት መክሊት ህንፃ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-01
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 011 667 2342 ማነጋገር ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባልስልጣን