Addis Zemen (Apr 07, 2026)
የምርት አከፋፋይነት ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001-2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ በክምችት የሚገኘው የእንስሳት መኖ ግብዓት (ኖራ) (CaCo3) እና የተፈጨ ኖራ (ፓወደር ላይም ስቶን) (አግሪ ላይም) በአጋርነት ከፋብሪካችን በመረከብ ምርቱን ለሚያከፋፍሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውክልና ለመስጠት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር ይችላል።
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ባቱ ከተማ ካለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኤምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ/ናሚቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200.00) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድና የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ምርቱ የሚገኝበት ባቱ ከተማ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ ድረስ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
4. ፋብሪካው ማንኛውንም ምርት ለሚረከቡት ተጫራቾች የዱቤ ከፍያ አገልግሎት አይሰጥም፡፡ በፋብሪካው የመሸጫ ዋጋ ቢያንስ በየምርት አይነት ከ500 ቶን ያላነሰ ክፍያ አስቀድሞ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የአገልግሎት አይነት ዋጋ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን የተሞላ ዋጋ በሌላ ድርጅት ላይ ተንተርሶ ከሆነና ስርዝ ድልዝ ያለው ወይም የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በፖስታ ታሽጎ እላዩ ላይ የተጫራቹ ድርጅት/ ግለሰብ ስምና አድራሻ በትክክል ተፅፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ ስም የተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በፖስታ ነጥሎ ያላቀረበ ተጫራች ሰነዱ ለውድድር አይቀርብም።
8. ተጫራች ያስያዘው የጨረታው ማስከበሪያ ለአሽናፊው ድርጅት ከሚከፍለው የስራ አፈጻጸም ዋስትና ላይ የሚቀነስለት ወይም ውል እንደተፈረመ የሚመለስ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታ አሸናፊ እንደታወቀ ይመለስላቸዋል።
9. ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ5 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ6ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ/ተዘግቶ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ኩዌት ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የማርኬቲንግ ማስተባበሪያ ቢሮ ይከፈታል።
10. የጨረታ አሸናፊዎች ተለይቶ እንደታወቁ ያሸነፉበትን ዋጋ ቀርበው ከከፈሉ በኋላ ቢበዛ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል ሆኖም ግን በመርሀ–ግብሩ መሠረት ምርቱን ማንሳት ካልቻሉ በውል ስምምነት በሚካተተው መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
አ.አ ስልክ ቁጥር 011-6-18-43-10 / 17
አ.አ ፋክስ ቁጥር 011-618-15-29
ባቱ ስልክ ቁጥር 046-441-34-15
ባቱ ፋክስ ቁጥር 046-441-24-63
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ