Reporter (Apr 08, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የ2017 በጀት አመት አጠቃላይ የተቋሙን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል::
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ የኦዲት ድርጅት በጨረታው ላይ እንድትሳተፋ ተጋብዛችኃል::
1. በኦዲት ሥራ ፈቃድ ያለው እና የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ያለው
2. የቲን ነበር የቫት እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው::
3. ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
4. የኦዲት ሥራው የሚከናወነው በIFRS እና በGAAP ሪፖርት አሰራር መሰረት መሆን አለበት::
5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ፊርማቸውን አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ አለባቸው::
6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል::
7. ማንኛውም ተጫራቾች ኦርጅናሉን የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተቋሙ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታው ሰነድ ገቢ መደረግ አለበት::
8. ጨረታው በተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በተቋሙ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል:: ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም::
9. የመክፈቻ ቀኑ የሕዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
10. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 025-112-48-20 / 09-35–63-18-73 ደውለው ይጠይቁ
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ
ድሬደዋ