Addis Zemen (Apr 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ለግብርና መካናይዜሽን አገልግሎት የሰጠውን ትራክተር ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውል መሰረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ ባለበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የተከራይ ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ |
የንብረቱ አይነት |
መነሻ ዋጋ (ብር) |
ሐራጁ የሚካሄድበት |
የሐራጁ ደረጃ |
||
|
ቦታ |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
|
ደረጀ ከፋለ ግብርና መካናይዜሽን |
ደብረማርቆስ ቅርንጫፍ |
ትራክተር |
5,660,542.58 |
ደብረማርቆስ ቅርንጫፍ |
ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:00-6:00 |
አንደኛ |
የሐራጁ መመሪያ፡–
1. በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመጀመሩ በፊት ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል በኩል ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል።
2. ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክለው በሐራጁ ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ እና ማሻሻያዎቹ(ካሉ)፤የንግድ ምዝገባ፤ የንግድ ፈቃድ፤ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም 25% በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) ብቻ አሰርተው ከጨረታው ቀን በፊት ማስያዝ ወይም ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ(CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
4. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ሐራጁ ከተካሄደበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።አሸናፊው ጨረታውን ያሸነፈበትን ገንዘብ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ለባንኩ መክፈል ይኖርበታል፡
5. አሸናፊ ተጫራች ንብረቱን በማሽነሪ ዱቤ ግዥ እና ኪራይ ውል ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ በባንኩ አሰራር መሰረት ከላይ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ በመከፈል የባንኩን የማሽነሪ ዱቤ ግዥ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የሽያጩን 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ የሚከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን የስም ማዘዋወሪያን ጨምሮ የጨረታው አሸናፊው ይከፍላል።አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸናፊው ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል።
7. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነፃ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነፃ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።
8. ተጫራቾች ትራክተሩ ያለበትን ይዞታ ለማየት ከፈለጉ አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን በፊት በቦታው በመገኘት መመልከት ይቻላል።
9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 058-178-6649
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት