የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትራክተር ባለበት ሁኔታ በድርድር መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትራክተር ባለበት ሁኔታ በድርድር መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 14, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ስማቸው ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ የተገለፁት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደንበኛ በሌዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የወሰዱትን የካፒታል ዕቃ ኪራይ ከፍያ በገቡት ውል መሠረት ኪራይ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በባንኩ ስም ተመዝግበው ለደንበኞቹ ተከራይተው የነበሩትን እና ባንኩ ከተከራዮች መልሶ የተረከባቸውን የካፒታል እቃዎች በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በተሻሻለው የካፒታል እቃ ኪራይ አዋጅ ቁጥር 807/2005 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባለበት ሁኔታ በድርድር መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተከራይ ስም

የሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)

የጨረታ ሁኔታ

የጨረታ ደረጃ

ድርድሩ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት

1

ሀጂ ኡስማን ኢብራሂም መሐመድ

አንድ ትራክተር ብራንድ SAME፤ የስሪት ዘመን 2017፤ አቅም 130 Hp፤ ስሪት ጣሊያን

  • አንድ መከስከሻ ባለ 28 ዲስክ
  • አንድ ማረሻ ባለ 4 ዲስክ

አፋር ክልል ሰመራ ከተማ

 

4,340,000.00 (አራት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ ሺህ ብር)

ድርድር

አንደኛ

 

ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00- 6:00 ሰዓት

 

ማሳሰቢያ፦

1, ተጫራቾች የጨረታው መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በማቅረብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

2. በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች የድርጅቱን መተዳደርያ ደንብ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ቅ/መ/ቤት የተሰጠ የውክልና ሰነድ እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ንብረቱን በገዢው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል። ገዢው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።

4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መከፈል ይኖርበታል። ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለጨረታ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ተሰርዞ በድጋሜ የድርድር ጨረታ ሽያጭ እንዲወጣ ይደረጋል።

5. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

6. የጨረታው አሸናፊ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወር ይከፍላል።

7. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል የካፒታል እቃ ኪራይ ብድር ነው።

8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ንብረቶቹ መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከጨረታው ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ንብረቶቹ በሚገኙበት ዲስትሪከት በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይችላል።

10. የድርጅቱ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆነ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አልያም የሚፈለገውን ቀረጥ ታክስ ለመንግሥት ለመክፈል ይገደዳል።

11. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሠመራ ዲስትሪክት ስልክ ቁጥር፦ 033 366 8612 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *