Melekite Dire (Apr 15, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በድሬደዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፑል በሥሩ ለሚገኙት ለመንገዶች ባለስልጣን ለጽዳትና ውበት ለቁራ አ/ ድርጅትና ለአውቶቢስ ክፍል ለ2018 በጀት ዓመት ለከባድና ቀላል መኪኖች የሚሆን ጎማ ና ካለመዳሪና ፍላፕ እና ለሞተር ሳይክል (ተሽከርካሪዎች የጎማ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል በመሆኑም በግልፅ ጨረታ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ የሚከተለውን መስፈርት የምታመሟሉ ተጋብዛችኋል
በጨረታው መወዳደር ለሚፈልጉ ተሣታፊዎች የጨረታው መስፈርት፡–
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ
3. የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
5. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በጥሬ ወይም CPO ማስያዝ ይኖርበታል
7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ እንዲሁም በአቅራቢው መሞላት ያለበት የዶክመንት ከፍል ሞልተው ተፈርሞ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ እንድታቀርቡ እያሳሰብን በመመሪያው መሰረት የማያቀርቡ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
8. ተጨራቾች የሚጫረቱባቸውን ሠነዶች ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9 ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀን ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ22ተኛ ቀኑ ይከፈታል፤ የጨረታ ሰነዱን 500 ብር በመክፈል ፋይናንስ ክፍል መግዛት ትችላላችሁ፡፡
10. ጨረታውን ሞልታችሁ የመለሳችሁ እለት በእዛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዛኑ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል 4፡00 ይከፈታል፡፡
ማሣሰቢያ፡– መ/ቤቱ በጨረታው የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ ከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ የስ/ቁ 09 15 75 53 24
አድራሻ፡– ድሬደዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ቢሮ ትራፊክ መብራት አጠገብ ከቴሌ ህንጻ ከፍ ብሎ፡፡