Addis Zemen (Apr 23, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጨ22/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት
- በድጋሚ የወጣ የፈተና ማሸጊያ ኮሮጆ፣ የፈተና ማሸጊያ ቁልፍ፣ ፈርኒቸር እና የኤሌክትሪክ እቃዎች
- የስፖርት ትጥቅ፣ የመኪና ጎማ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች(ከለር ፕሪንተር እና ፕሪንተር) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫሮቾች፡–
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባው።
- ጨረታው በግልጽ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል። ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በአባይ ባንክ ወይም ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውስድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ በድጋሚ የወጣ የፈተና ማሸጊያ ኮሮጆ 20000.00/ ሃያ ሺህ ብር/፣ የፈተና ማሸጊያ ቁልፍ 20000.00/ሃያ ሺህ ብር/፣ ፈርኒቸር 20000.00/ሃያ ሺህ ብር/፣ የስፖርት ትጥቅ ብር 10,000.00፣ ‘የመኪና ጎማ ብር 50,000.00፣ የኤሌክትሪክ እቃ ብር 20,000.00 እና የኤሌክትሮኒክስ እቃ(ከለር ፕሪንተር እና ፕሪንተር ብር 50,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ።
- የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታዉ ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል።
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያአዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል። አዳራሹ በስብሰባ ከተያዘ መረጃ ዴስክ ወይም ኮሪደር ልማት አካባቢ ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብክመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 6267 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አቅራቢ ድርጅቶች ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የቢሮው ገንዘብ ያዥ ግራውንድ ቢሮ ቁጥር 15 በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ