የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የክልሉ ንብረት የሆነውን በክልሉ ገንዘብ ቢሮ ግቢ፣ በተለያዩ የዞን መአከሎች የተለያዩ ጋራጆች ውስጥና በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የክልሉ ንብረት የሆነውን በክልሉ ገንዘብ ቢሮ ግቢ፣ በተለያዩ የዞን መአከሎች የተለያዩ ጋራጆች ውስጥና በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 23, 2026)

የሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡አፋር ንብ ማስ// //ተሽ/13/08/2018

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የክልሉ ንብረት የሆነውን በክልሉ ገንዘብ ቢሮ ግቢ፣ በተለያዩ የዞን መአከሎች የተለያዩ ጋራጆች ውስጥና በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ለመመዝገብ ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ 2018 . የታደሰ ሰነድ ወይም ናሽናል አይዲ [National ID] ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ሲፒኦ አስገብተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 14 ቀናት ውስጥ ብቻ ከጠዋቱ 230 እስከ ከሰኣት 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣

3. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ እንዲሁም የስም ዝውውር፣ እና ሌሎች ወጪዎች ካለበት ያለበት ሁነው ወጭ በገዥው ይሸፈናል፣

4. ተጫራቾች ለሚገዙት ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 150,000ብር (አንድ መቶ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታ ከመጀመሩ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከሰመራ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣

5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን፤ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክልሉ ገንዘብ ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለክልሉ መንግስት ገቢ ይደረጋል።

7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን ያሻነፈበት ጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሸከርካሪውን 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣

9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 251-33 -366 6767 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣

10. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

ሰመራ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *