በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ስር በቻግኔ ሴክሸን ላይ ተክሎ ያሳደጋቸውን ባህር ዛፍ እና የተለያዩ ዛፎች ብዛት 692 ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ስር በቻግኔ ሴክሸን ላይ ተክሎ ያሳደጋቸውን ባህር ዛፍ እና የተለያዩ ዛፎች ብዛት 692 ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 25, 2026)

በድጋሚ የወጣ የዛፍ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 05/2018

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ስር በቻግኔ ሴክሸን ላይ ተክሎ ያሳደጋቸውን ባህር ዛፍ እና የተለያዩ ዛፎች ብዛት 692 ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የታደሠ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ ተጫራቾች አስፈላጊውን ማስረጃ በማያያዝ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ዛፎቹን በቦታው በአካል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 230 እስከ 1130 ሰዓት ድረስ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በኢ.. ንግድ ባንክ አካውንት (ERAD/M/R/M/D_Account No.1000322269165) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል። ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ያላነሰ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ዋና (Original) እና ኮፒ (Copy) ሠነዱን ለየብቻው አሽጐ በአንድ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 200 እስከ 1100 ሰዓት በዲስትሪክቱ ግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን በመውሰድና በጥንቃቄ በመሙላት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን 16ኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ታሽጐ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በእሁድ ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

4. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለተሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ይመለሳል።

5. የጨረታው አሸናፊ በፅሑፍ እንደገለፁለት ወዲያውኑ በአካል ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት። ይህን ባይፈፅም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

6. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ገንዘብ ክፍያ በመፈፀም ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል።

7. ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ፡በስልክ ቁጥር– 058 771 3052 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *