Addis Zemen (Apr 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ ሐራጅ ጨረታ ቁጥር 16/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ–ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ)፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ poly(ethylene terephtalate) plastic cas (ጥሬ ፕላቲክ) ፣ኮስሞቲክስ፣ fabric rope፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እና አዳዲስ አልባሳት በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡– ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን።
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡–
1.ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
4. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
5. በሐራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 01, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩልዩ) ብር 77,800.00፣ ለምድብ 02, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 12,900.00 ለምድብ 03, ኤሌክትሮኒክስ ብር 211,200.00 ለምድብ ዐ4, ኤሌክትሮኒክስ ብር 72,000.00 ፣ለምድብ 05, ኤሌክትሮኒከስ ብር 67,500.00 ለምድብ 06, poly (ethylene terephtalate) plastic cas (ጥሬ ፕላቲክ) ብር 67,600.00 ለምድብ ዐ7, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 33,300.00 ፣ለምድብ ዐ8, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 191,500.00 ለምድብ 9, ኮስቲክስ ብር 110,200.00፣ ለምድብ 10, ኮስሞቲክስ ብር 114,000.00፣ ለምድብ 11, ኮስሞትክ ብር 406,400.00፣ ለምድብ 12, fabric rope ብር 69,100.00፣ ለምድብ 13, ኤሌክትሮኒክስ ብር 47,000.00፣ ለምድብ 14, ኮስሞቲክስ ብር 116,000.00፣ ለምድብ 15 ኤሌክትሮኒክስ ብር 156,100.00፣ ለምድብ 16, የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ብር 213,500. ለምድብ 17, ኤሌክትሮኒክስ ብር 616,400.00፣ ለምድብ 18, አዳዲስ አልባሳት ብር 14,800.00 እና ለምድብ 19, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 5,000.00 (Customs Commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
6. በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማየት እና መጫረት ይቻላል።
7. በሐራጅ ጨረታ የእቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
11. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12.ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራች ቢያሸንፍ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግ እና እቃው በድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።
የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55 11/011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡– አዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት