Addis Zemen (Apr 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢንሀንሲንግ ፓስተራሊስት ሪሰርች ኤንድዴቬሎፕመንት ኦልተርኔቲቭስ (ኤፓራዶኦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን አንድ ያገለገለ መኪና ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። መኪናው የተሰራበት ዘመን እ.ኤ.አ. 2008 የሆነ ቶዮታ ሎንግ ቤዝ (Toyota Long Base) ነው።
ተጫራቾች
1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ከታች በተገለጸው አድራሻ በመገኘት መኪናውን መመልከት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የሚገዙትን መኪና ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ው ለሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።
4. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለፀቸው ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ሙሉ ገንዘቡ ገቢ በማድረግ በ 10 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
5. ተጫራቾች ከድርጅቱ የመኪናውን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የያዘ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት (እስከ ሚያዚያ 29/2018) ከጠዋቱ 3፡00 እሰከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በ11ኛው (ሚያዚያ 30/2018) ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
6, የመኪናውን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ የሚለው አምድ /column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ፣ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ ፖስታ ከታች በተገለፀው አድርሻ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እሰከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን (ሚያዚያ 30/2018) በ9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 9፡30 ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድርጅቱ በተዘጋጀው ቦታ ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
9. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በቅሎ ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ
ስልክ ቁጥር +251 91 156 6127
+251 95 110 3615
ኢንሀንሲንግ ፓስቶራልሊሰት ሪሰርች ኤንድ ዲቬሎፕመንት ኦልተርኔቲቭስ