Addis Zemen (Apr 25, 2026)
ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎች እና ያገለገሉ የተሸከርካሪ ባትሪዎች
የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥC DIS 01/2018
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በድርጅቱ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅርንጫፍ፤ በሚሌ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጥገና ማዕከል እና በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል አገልግለው የተመለሱ ንብረቶችን ማለትም በድርጅቱ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅርንጫፍ እና በሚሌ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጥገና ማዕከል የሚገኙ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጎማዎችን እና አገልግለው የተመለሱ የመኪና ባትሪዎችን እንዲሁም በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል አገልግለው የተመለሱ የወደብ መገልገያ ማሽነሪ ጎማዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታ ሂደቱ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት/ግለሰብ የንግድ ምዝገባ፤ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፊኬት እና ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች ከአካባቢ ጥበቃ አኳያ በዘርፉ ለተሰማሩ እና ከሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ ወይም ከሚመለከተው የከተማ አስተዳደር/ክልል አካባቢን ሳይበክል መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ስለመሆኑ ፍቃድ ያለው ወይም የፅሁፍ የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የተመላከቱትን አስገዳጅ ዝርዝር መመዘኛዎችን ሟሟላት የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ሚያዚያ 17 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ማክሰኞ ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ህዝባዊና ኃይማኖታዊ ባዕላትን ጨምሮ በሚቆጥር ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ በመከፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል።
ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች በቃሊቲ ትራኪንግ እና በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡ዐዐ እስከ 6፡0 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ሰነድ የገዙበትን ማስረጃ በማሳየት መመልከት ይችላሉ።
ጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እና የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ማክሰኞ ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከ8፡ዐዐ ሰዓት በፊት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ወይም በኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 554 9304/ 09 06 32 90 86 Web ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ