ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አልባሳት፣ ጫማ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ኮስሞቲክስ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ምግብ ነክ እና ተሽከርካሪ በግልፅ እንዲሁም ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች እና Woven bag በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አልባሳት፣ ጫማ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ኮስሞቲክስ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ምግብ ነክ እና ተሽከርካሪ በግልፅ እንዲሁም ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች እና Woven bag በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር -27/2018 ዓ.ም.

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ /ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ

  • አልባሳት፣ ጫማ፣
  • የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣
  • ኮስሞቲክስ፣
  • የኤሌክትሪክ እቃዎች
  • ምግብ ነክ እና ተሽከርካሪ በግልፅ እንዲሁም
  • ኮስሞቲክስ፣ተሽከርካሪ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች እና
  • Woven bag በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡

1) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር /ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛዉም እድሜዉ 18 አመት በላይ የሆነ የኗሪነት መታወቂያ ያለዉ ግለሰብ መጫረት ይችላል፡፡

2) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር /ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል፡፡

3) የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋዉ ከብር 2 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛዉንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡

4) በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይምየባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡

5) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ /ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 0300 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

6) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ /ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 350 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡

7) ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩከ ኮሚሽን ኮምቦልቻ //ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታዉ 350 ሰዓት ተዘግቶ 400 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታው 430 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል፡፡

8) ተጫራቾች በጨረታዉ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡በተሰጠው የጊዜገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃዉ እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡

9) ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሽናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡

10) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ //ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት እስከ 1000 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 300 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡

11) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሐራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ 2 ሚሊየን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 መቶ ሺህ ብር እንዲሁም የእቃው መነሻ ዋጋ 2 ሚሊየን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 መቶ ሺህ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

12) መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት