የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የወላይታ ሪጅን የተለያዩ ያገለገሉ በኬሚካል የተነከሩ የእንጨት ምሰሶዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የወላይታ ሪጅን የተለያዩ ያገለገሉ በኬሚካል የተነከሩ የእንጨት ምሰሶዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 30, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ወ/ሪ/ግ/ቴ/005/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የወላይታ ሪጅን የተለያዩ ያገለገሉ በኬሚካል የተነከሩ የእንጨት ምሰሶዎች ሽያጭ ከዚህ በታች ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ

ጨረታው የሚዘጋበት

ጨረታ የሚከፈትበት ቀን

1

ያገለገሉ የእንጨት ምሰሶ

በሜትር ኪዩብ

400

5,000.00

ሚያዝያ 19/2018 8:00

ሚያዝያ 28/2018 8:30

ማሳሰቢያ፡- የእንጨት ምሰሶው በኬሚካል የተነከረ ስለሆነ ለማገዶ መጠቀም የማይቻል መሆኑን እንድታውቁ እናሳስባለን።

1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ሚያዝያ 19/08/2018 ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ወላይታ ከተማ በተለምዶ ስም አብረሃም ሆቴል ጎን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ወላይታ ሪጅን ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) አካውንት ቁጥር 1000254810995 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /cpo/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (bid Security) በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሚያዚያ 28/08/2018 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ወላይታ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ሚያዚያ 28/08/2018 ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ላይ ይከፈታል።

4. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 046-180-6012 / 09 49 24 75 19 መደወል ይችላሉ።

5. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

ወላይታ ሪጅን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *