በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሸቀጣ ሸቀጥ (ልዩ ልዩ)፣ መነፅር (የእይታ መሳሪያ) እና ምግብ ነክ በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሸቀጣ ሸቀጥ (ልዩ ልዩ)፣ መነፅር (የእይታ መሳሪያ) እና ምግብ ነክ በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 04, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 17/2018 .

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ //ቤት በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሸቀጣ ሸቀጥ (ልዩ ልዩ) መነፅር (የእይታ መሳሪያ) እና ምግብ ነክ በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et

ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።

3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 200-600 ሰዓት መመልከት ይቻላል።

4. በግልፅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የእቃዎቹ አስመጪ ወይም የአስመጪ ቤተሰብ መሳተፍ አይችሉም። ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

5. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5 %) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs Adama Branch) ስም ብቻ ... በማሰራት ያሰሩትንም ... በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን አክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

6. በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ /ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ ለግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 400 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 / ሶሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

9. ከላይ በተ/ 8 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

10. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።

11. //ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09- 05-11-55 11 / 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃ፡አዳማ ///ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ //ቤት