Addis Zemen (May 06, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ለእንስሳት ምጥን መኖ ዝግጅት የሚያስፈልግ ጥሬ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ TIN ሰርትፍኬት የሚያቀርቡ፣ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በአቅራቢነት የተመዘገቡ ሆነው፡-
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል መግዛት የሚቻል መሆኑን፣
- የጨረታ ሰነድ ኦሪጂናልና የኦሪጂናል ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማዘጋጀት የጨረታ ሳጥን ከመታሸጉ በፊት በጨረታ ሳጥን መጨመር ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ይገኛል።
ተጫራቾች የሚሰጡትን ዋጋ መነሻ በማድረግ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን አሸናፊው በውሉ መሠረት ምጥን መኖውን እስከሚያስረክብ ድረስ ተይዞ ይቆያል።
በጨረታዉ ተሸናፊዎች ያስያዙትን ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከተጠናቀቀበት ከ7 (ሰባት) ቀናት በኋላ ይመለስላቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ጨረታውን ላሸነፈ ተጫራች ማዕከሉ ቅድመ ክፍያ አይፈጽምም ነገር ግን አሸናፊው በውሉ
- መሠረት ምጥን መኖውን ካስረከበ በኋላ ክፍያው ወድያውኑ ይፈፀማል።
- ማዕከሉ በጨረታ ሰነድ ላይ ከተገለጸው መጠን ከጠቅላላው በ20% ቀንሶ ወይም ጨምሮ የመግዛት መብት አለው።
- የጥሬ ዕቃው መጫኛ፣ እስከ ማዕከሉ ማጓጓዣና ማውረጃ ወጪ በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈን ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ውል ከገባበት ዕለት ጀምሮ ዐ7 (ሰባት) ቀናት ውስጥ ጥሬ ባሉት ዕቃውን ማስረከብ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖርና የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀን በአየር ላይ ይውልና የሚቀጥለው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በ4፡00 ሠዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ይከፈታል።
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916285340፣ 0911612578 እና 0911575873 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የወላይታ ሶዶ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል