የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተር እና የእርሻ ማረሻ በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተር እና የእርሻ ማረሻ በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 07, 2026)

የመጀመሪያ (1) ዙር የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኛ የወሰደውን የካፒታል ዕቃ ኪራይ ክፍያ በገባው የሊዝ ውል መሠረት ኪራይ ለመክፈል ፍቃደኛ ባለመሆኑ በባንኩ ስም ተመዝግበው ደንበኛው ተከራይቶ የነበረውን እና ባንኩ ከተከራዩ የተረከባቸውን የካፒታል ዕቃዎች በሊዝ አዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በተሻሻለው የካፒታል ዕቃ ኪራይ አዋጅ ቁጥር 807/2005 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በመጀመሪያ (1 )ዙር በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተቁ

የተከራዩ ስም

የሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ (በብር)

ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ

ሐራጅ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

አቶ አበበ ሃዋዴ የእርሻ መካናዜሽን አገልግሎት መስጫ

1. የእርሻ ትራክተር (በቁጥር 01) ብራንድ Massey Ferguson የሰሪት ዘመን 2021 አቅም 112HP እና ሞዴል MF67 11

2. የአርሻ ማረሻ (በቁጥር 01) ብራንድ OTMA የስሪት ዘመን 2019 ሞዴል O/QD70/E

የኢትዩጵያ ልማት ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ነው::

5,661,442.97

የኢትዩጵያ ልማት ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት /ቤት ግቢ ውስጥ

ሰኔ04 2018 /4:00 እስከ 6:00

የሐራጅ መመሪያ

  1. የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ .. በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይቻላል። በድርጅት ሰም የሚጫረቱ ተጨራቾች የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ /ቤት የተሰጠ የውክልና ሰነድ እና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በማቅረብ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሐራጅ ጨረታው ይካሄዳል።
  2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግሥት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በሐራጅ ጨረታው መሳተፍ ይችላል፤
  3. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አሰራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውሰጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል።ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጅ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጅ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል።በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፤
  4. ማንኛውም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የንግድ ፈቃድ ያለው፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ በሐራጅ ጨረታ መሳተፍ ይችላል።
  5. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል ።ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግሥት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል።
  6. ንብረቱ በገዥው ስ እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  7. በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት .. ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  8. ባንኩ ለሸያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው እጅ በእጅ በሚደረግ ሽያጭ/cash/ ወይም በባንኩ የሊዝ ፖሊሲ አሠራር በመከተል የሚደረግ ሸያጭ ይሆናል።
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከጨረታው ቀን በፊት ባሉት ጊዚያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በሐዋሳ ዲሰትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-180-1528 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *