Addis Zemen (May 09, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አፈፃፀም ከሳሽ– ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአፈፃፀም ተከሳሽ– ፍሊንትስቴን ኢንጅነሪንግ መካከል ባለው የአፈፃጸም ክርክር ጉዳይ፤በተከሳሽ ድርጅት ፍሊንትስቴን ኢንጅነሪንግ ወይም ባለቤት ፀደቀ ይሁኔ ወልዱ ስም የተመዘገበ ዊል ሎደር ማሽን አፈ/ተከሳሽ ስም የተመዘገበው በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሳይት ውስጥ የሚገኘው ማሽን በግልጽ ጨረታ በመነሻ ግምቱ ዋጋ ብር 1,160,651.40 አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ ሺ ስድስት መቶ አምሳ አንድ ብር ከአርባ ሳንቲም ሆኖ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በጨረታ እንዲሸጥ የአብከመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ በሰጠው መሰረት በመመደብ የአማራ ክልል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያም ፀጥታውን የሚያስከብር አንድ ሰው በመመደብ የጨረታው ስነ–ስርዓት በአግባቡ እንዲከናወን እንዲደረግ ሆኖ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሐራጅ ባይም ጨራታውን በበላይነት በመምራት ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሳይት ውስጥ በመሆኑ ማሽኑን ለመግዛት መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከቦታው በመገኘት ምልከታ አድርጐ ቀርቦ ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ መጫረት መሳተፍ የሚቻል እና አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ከተቻለ ሙሉውን ገንዘብ የሚያስይዝ ካልተቻለም አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ለፍ/ቤቱ ሐራጅ ባይ በሲፒኦ የመክፈል ግዴታ ያለበት ሲሆን ጠቅላላ ዋጋውን በሃያ ቀናት ውስጥ ሲያጠናቅቅ ማሽኑን መረከብ የሚችል መሆኑን እንዲያውቁት የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት አዟል፡፡
የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት