Addis Zemen (May 26, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ከፍያ ፈፅሞባቸው ከደንበኞቹ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫዕቃዎች እና ኢንሹራንሱ ሲገለገልባቸው የነበሩ ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ ቁሳቁሶችንና ሌሎችንም ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- * በመሆኑም እነዚህን ዕቃዎች ለመግዛት የምትፈልጉ ሁሉ ቃሊቲ ከሸገር ዳቦ ጎንና ቃሊቲ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የኩባንያችን የተጎዱ ተሸከርካሪዎች ማቆያ (ሪከቨሪ) በመገኘት እና በማየት የምትገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቭሎፕ ከግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብሔራዊ ትያትር ጀርባ በሚገኘው አዋሽ ታወርስ የኩባንያው ዋና መ/ቤት እንግዳ መቀበያ ድረስ በመቅረብ የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ጨረታው ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ቃሊቲ ከሸገር ዳቦ ጎን በሚገኘው የኩባንያችን ሪከቨሪ ይከፈታል።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም። ተጫራቾች የመነሻ ዋጋቸው እስከ 5,000 ለሆኑት ብር 500፣ ከብር 5,001 እስከ ብር 10,000 ለሆኑት ብር 2,000 ከብር 10,001 እስከ 50,000 ለሆኑት ብር 5,000 ፣ ከብር 50,000 በላይ ለሆኑት የመነሻ ዋጋውን 10% /አስር በመቶ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ሁሉም የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ከተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ውጪ ሞልተው የሚያቀርቡት ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።
- ከጨረታው በኋላ ያሉትን ወጪዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል።
- አሸናፊዎች ንብረቶቹን ጨረታው ከተካሄደበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ከፍያውን ፈጽመው ካልተረከቡ ጨረታው የሚሰረዝ ከመሆኑም በላይ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ አይደረግም፣ በሌላ በኩል ክፍያ ፈፅመው ዕቃዎቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ቢሆን ኩባንያው ኃላፊነት የለበትም።
- በአዋጅ ቁጥር 681//2010 አንቀፅ 6 (3) በተደነገገው መሠረት ጥገና ለሚከናወንባቸው ተሽከርካሪዎች የተሸከርካሪው የባለቤትነት ስም እንዲዛወርለት በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት ማመልከት ይኖርበታል።
- ኢንሹራንሱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ.
01 557 00 01
ፋክስ 011 557 0208
011 557 0218
የሪከቨሪ 011 439 1101
ፖስታ ሳ.ቁ 0012637
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ