የጂንካ ማረሚያ ተቋም ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል የምግብ እህሎች፤ ቅመማ ቅመም፤ አትክልት እና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጂንካ ማረሚያ ተቋም ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል የምግብ እህሎች፤ ቅመማ ቅመም፤ አትክልት እና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 06, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጂንካ ማረሚያ ተቋም ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል የምግብ እህሎች፤ ቅመማ ቅመም፤ አትክልት እና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዚሁ ዘርፍ የተሰማራችሁ ተጫራቾች (ነጋዴዎች) ከዚህ በታች በወጣው ማስታወቂያ ዝርዝር መስፈርት መሠረት ቀርባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።

የተጫራቾች መስፈርት፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው (ያላት)

2. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር ያለውና መረጃውን ማቅረብ የሚችል

3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማረጋገጫ የሚያቀርብ

4. የታደሰ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅርብ የሚችል

5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለበቆሎ፣ ጤፍ፣ ፊኖ ዱቄት፤ አተር ክክ፣ ካሳባና ማገዶ እንጨት ለእያንዳንዱ 100,000/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ጨው፣ በርበሬ፣ ሽንኩርት፤ እርሾና እርድ ለእያንዳንዱ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO (በጥሬ ገንዘብ) በቅድምያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ዋጋ 50 ብር /ሃምሳ ብር/

8. የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ጂንካ ማረሚያ ተቋም ቢሮ ቁጥር 4

9. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄደው የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ2፡00 እስከ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱ በጨረታ ሳጥን ወስጥ የሚገባ ሲሆን በእለቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

10. የእቃው ርክክብ የሚፈፀምበት ቦታ ጂንካ ማረሚያ ተቋም

ማሳሰቢያ፤

ሀ/ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 046 875 9067
የጂንካ ማረሚያ ተቀም


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *