Reporter (Jun 28, 2026)
ጨረታ ቁጥር AMREF_ ET/26/06/2026-0018
የጨረታ ማስታወቂያ
አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ (Amref Health Africa in Ethiopia) አለም አቀፍ ግበረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን
- ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል::
- የጨረታውን ሰነድ ስለመግዛት፡– ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 በሚከተለው የአካውንት ቁጥር ገቢ አድገው የባንክ ደረሰኝ/deposit slip በማቅረብ ሰነዱን ከድርጅቱ ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ (ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ፣ ከሰዓት ከ7፡30-11፡00) አርብ (ጠዋት ከ2፡30-6፡30) አስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መውሰድ ይችላሉ:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ/ የባንክ አካውንት ቁጥር-1000131778868 የአካውንት ሥም– አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ/Amref Health Africa የጨረታው ሰነድ ዋጋ– ብር 500.00
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ (ጠዋት ከ2፡30-6፡30፣ ከሰዓት ከ7፡30-11፡00) አርብ (ጠዋት ከ2፡30-6፡30) የሚሸጡትን ያገለገሉ እና ጥገና የሚፈልጉ ተሽከርካሪዎችን አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ ቀርበው አስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መመልከት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ሊገዙ ለሚፈልጉት ተሽከርካሪ/ዎች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ሰነድ ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማለትም አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅጽር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ለጨረታ በተዘጋጄ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበቸው ተሽከርካሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ/ Amref Health Africa in Ethiopia ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ፖስታ ውስጥ አብሮ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ማከስኞ ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው:: በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድቦንድ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል:: የጨረታ አሸናፊዎች ያገለገሉ ተሽከርሪዎች ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ወጪዎች፤ የማጓጓዣ ወጪዎችንና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችን ይሸፍናሉ::
- በጨረታው ለሚሸነፉት ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ የጨረታ አሸናፊው ሙሉ ክፍያውን እንደፈጸመ የሚመለስላቸው ይሆናል::
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ
አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ቦሌ መድኃኒአለም ቤ/ክ ጀርባ
ከአቢሲኒያ ሕንፃ ጐን፣ አምረፍ ሔልዝ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅጥር ግቢ ውስጥ
ስልክ፡ 0116627851 ወይም 0911 1 449 61/0911 165913