Reporter (Jun 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ለሶስተኛ ጊዜ ለመሸጥ የተዘጋጀ ሽያጭ DB/049/2018
ዳሽን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለሶስተኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች ቄራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል በመምጣት የጨረታውን መረጃ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በባንኩ መጋዘኖችና ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው::
- ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል::
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከዳሽን ባንክ አማ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣ ሆኖም በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ክፍያ በቶሎ ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ክፍያው በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በተዘጋጀ ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል::
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 8 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በ8ኛው ቀን ማለትም ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ06፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ09፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ባንኩ የንበረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም::
- በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ3 /ሶስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 /ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል:: ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ካልፈረሙ ወይም ሙሉክፍያውን በተጠቀሰው ግዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል::
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ውል በፈረሙ በ10 የሥራ ቀናት ዉስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
- ባንኩ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል::
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-4655552፣ 011-4706065 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
- ባንኩ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ዳሽን ባንክ አ.ማ.
አዲስ አበባ
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
Managerial Table |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
2 |
Computer stand and coffee table |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
3 |
Lowback chair |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
4 |
Guest chair |
በጥቅል |
በጥቅል |
|
5 |
Gun Box |
በቁጥር |
5 |
|
6 |
Monitor |
በቁጥር |
25 |
|
7 |
Note Counting Machine |
በቁጥር |
124 |
|
8 |
Multi-currency Detector |
በቁጥር |
11 |
|
9 |
Adding Machine |
በቁጥር |
20 |
|
10 |
Scanner |
በቁጥር |
49 |
|
11 |
Wall clock |
በቁጥር |
5 |
|
12 |
Metal Detector |
በቁጥር |
60 |
|
13 |
Lost and found display |
በቁጥር |
39 |
|
14 |
Notice Board |
በቁጥር |
24 |
|
15 |
HP LaserJet Printer |
በቁጥር |
9 |
|
16 |
Kyocera Printer |
በቁጥር |
33 |