Addis Zemen (Jun 30, 2026)
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን የካራት ከተማ አስተዳደር ካራት ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች በጨረታ በሽያጭ ለማስወገድ ስለሚፈልግ በጨረታ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች/ ድርጅቶች፡–
1/ በዚህ የሺያጭ ጨረታ ማንኛዉም ሕጋዊ ሰዉነት ያለዉ ግለሰብ ወይም ድርጅት ወይም ማህበር በጨረታዉ መሳተፍ ይችላል።
2/ በጨረታዉ የሚሳተፍ ተጫራች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ለድርጅቱ በመክፈል ሠነዱን መግዛት ይችላል።
3/ ተጫራች የሚወዳደርበትን ንብረት በየሎቱ ንብረቶቹ ወደ ሚገኙበት ቦታ ድረስ በመሄድ እና በመመልከት ወደ ጨረታዉ መግባት ይጠበቅበታል።
4/ ማንኛዉም ተጫራች በሚወዳደርበት ሎት ላይ ባሉ ንብረቶች በመነሻ ዋጋ በተቀመጠዉ ዋጋ በማስላ 3 (ሦስት) በመቶ የጨረታ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅበታል። የሚያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ የገቢ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ጨረታዉ እስከሚከፈትበት ሰዓት ድረስ ማስያዝ ይችላሉ።
5/ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዣ ለተሸናፊ ተጫራች ወዲአውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ተጫራች ግን ያሸነፈበትን ዋጋ ገንዘብ በድርጅቱ መደበኛ አካዉንት ገቢ ሲያደርግ የሚመለስ ይሆናል።
6/ አሸናፊ ተጫራች ከላይ በጨረታ ማስከበሪያነት ያስያዘዉን 3 (ሦስት) በመቶ የጨረታ ዋስትና ማስያዣ አሸናፊነቱ በተገለጸ በ 10 ቀናት ጊዜ ዉስጥ ሙሉዉን ከፍያ የማጠናቅቅ ከሆነ ማስያዣዉ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
7/ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ንበረቶች ምን ምን እንደሆነ በጨረታዉ ሰዓት በሚዘጋጅ ቅጽ መሰረት ለይቶ ማሳወቅ ይኖርበታል።
8/ ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳባቸዉን በፖስታ በማሸግ ሲሆን በእያንዳንዱ ንብረቶች ከተመዘገቡ ሌሎች ተጫራቾች ጋር መነሻ ዋጋን መሰረት በማድረግ የተሻለ ዋጋ ጥሪ በማድረግ እና በመፎካከር የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል።
9/ የጨረታዉ አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ በድርጅቱ የተዘጋጀዉን እንደዉል መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ቅጽ ይፈርማል። ወዲአሁኑ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከድርጅቱ ይደርሰዋል።
10/ አሸናፊ ተጫራች የአሸናፊነት ማሳወቂያ ደብዳቤ በደረሰዉ በ 10 ቀናት ዉስጥ ሙሉዉን ክፍያ በመክፈል ንብረቶችን መረከብ (ማንሳት) ይችላል።
11/ መ/ቤቱ ለእያንዳንዱ የንብረት ዓይነት በቂ ተጫራች አልቀረበም ብሎ ሲያምን በጥርጣሬ የሚያስገቡ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ጨረታዉን መሰረዝ ይችላል።
12/ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በጨረታ የሚወገዱ ንብረቶች ዝርዝር የያዘውን የመወዳደሪያ ሰነድ ከካራት ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት ፋይናንስ ንብረት አስ/ር በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
13/ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
14/ የጨረታው ሣጥን የሚታሸገዉ በ16ተኛው የሥራ ቀን 8፡00 ሲሆን የሚከፈተዉ በዚሁ ዕለት ልክ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
15 ጨረታዉ ይከፈታል በተባለበት በ16ኛዉ ቀን በመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
16/ በጨረታዉ ላይ ለመወዳደር የሚትፈልጉ ዕጩ ተጫራቾች የንብረቱ ዝርዝር የያዘ ፋይናንሻል ወይም የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ በአንድ ኤንቨሎፕ ወይም እናት ፖስታ የሚቀርብ ሆኖ ዋናዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለብቻ፣ ኮፒ የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለብቻ፣ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ፣ ስም፤ ፊርማ እና አድራሻ በመግለጽ በአንድ እናት ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
17/ ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ–ሥርዓትን አያስተጓጎልም።
18/ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ፡– / 09-16-15-53-35 / 09-16-70-81-96 / 09-82-54-35-33 ላይ ደውለው ያገኙን፤
በደ/ኢ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን የካራት ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት