Reporter (Jun 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ፡
የቢሮ ዕቃ ማዛወር አገልግሎት ግዥ
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሁኑ ቦታው (ቦሌ ድልድይ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት) ከሚገኘው ቢሮ አዲስ ወዳስገነባው ዋና መ/ቤት አድራሻ (አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት፣ ደጃዝማች ውቤ አካባቢ) ለማዛወር ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፣ ኩባንያው የቢሮ ዕቃዎችን (ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ የኮምፒውተርና የሰርቨር ዕቃዎችን ወዘተ) እና የተለያዩ የኩባንያውን ሰነዶች በጥንቃቄ በማሸግ፣ በመጫን፣ በማጓጓዝ እና በማውረድ/በማደራጀት የተረጋገጠ ልምድ ያላቸውን ብቁ ድርጅቶች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡
ከተጫራቾች የሚጠየቁ መስፈርቶች፡
1. ተጫራቾች ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት የ5 ዓመት ልምድ እና አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
3. ተጫራቾች አስፈላጊ የሆኑ የማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን እና የማሸጊያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ አቅም ሊኖራቸው ይገባል።
4. ተጫራቾች ስራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ የሚያሳይ የሥራ መርሃ ግብር ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ፡ ተጫራቾች 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ያለ ቅድመ ሁኔታ በሚፈጸም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማቅረብ አለባቸው።
6. አገልግሎት ሰጪው በእንቅስቃሴው ሂደት ለሚደርስ የሰነድ መጥፋት ወይም ጉዳት የኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል።
የጨረታ ሂደት፡
- የጨረታ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ድልድይ የቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው 3ኛ ፎቅ የኩባንያው የፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ፣ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስረከቢያ፡ የተሟላ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ፡ ጨረታው ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የኩባንያው መብት፡ ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የቢሮቹን ጉብኝት፡ ተጫራቾች የሁለቱንም ሕንፃዎች አቀማመጥ እና የሚዛወሩ ዕቃዎችን አይነትና መጠን ለመገምገም የሚያስችል የቅድመ–ጨረታ የጉብኝት ፕሮግራም ከ22/10/2018 -28/10/2018 በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል::
አድራሻ፡– ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ድልድይ፣ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ስልክ: +251 111 119 70 / +251 116 50 66 30