የምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ከመደበኛ በጀት ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ እህል፣ የባልትና ዉጤቶችን፣ መድሃኒት እና የማገዶ እንጨት መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ከመደበኛ በጀት ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ እህል፣ የባልትና ዉጤቶችን፣ መድሃኒት እና የማገዶ እንጨት መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Jun 29, 2026)

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ከመደበኛ በጀት ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ እህል፣ የባልትና ዉጤቶችን፣ መድሃኒት እና የማገዶ እንጨት አጫርቶ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን

  • ሎት አንድ 1. ቀይ ጤፍ፣ 2. በቆሎ፣ 3. ነጭ ሌሌ ማሽላ፣ 4. ጅሁላ ማሽላ፣ 5. ደበር ማሽላ
  • በሎት ሁለት የባልትና ዉጤቶች ማለትም 1. የተዘጋጀ ሽሮ፣ 2. የምግብ ዘይት፣ 3. የምግብ ጨዉ፣ 4. እርሾ፣ 5. ጎመንዘር እና ፊኖ ዱቄት፣
  • ሎት 3 መድሃኒት እና
  • ሎት 4 የማገዶ እንጨት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ የሆነዉን አቅራቢ ድርጅት ለ11 ወር ከነሀሴ 1/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ
    30/2019 ዓ.ም ዉል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. የሚገዙ የእህል፣ የባልትና፣ የመድሃኒት እና የማገዶ እንጨት አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የእህል፣ የባልትና፣ የመድሃኒት እና የማገዶ እንጨት ዉጤት 1.5 በመቶ (በሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመሂ 1 ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ማለትም ከሰኔ 22/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 06/2018 ዓ.ም ድረስ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳዉ ዉሃ ማረምያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን በመቅረብ ከ1-3 ያሉ ሰ ነዶችን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ ፡፡
  5. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 15 ቀን ቆይታ በኋላ በ16 ኛው ቀን ማለትም ሐምሌ 07/2018 ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉኃ ማረሚያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ስለሆነ ሁሉንም በሎት 1. የተቀመጠዉን የእህል ዋጋ፣ በሎት 2. የተቀመጠዉ የባልትና ዋጋ፣ በሎት 3 የተቀመጠዉን የመድሃኒት ዋጋ እና በሎት 4 የተቀመጠዉን የማገዶ እንጨት ዋጋ ለየራሳቸዉ መሙላት አለበት፡፡ ካልተሞላ ግን ከጨረታ ዉጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  7.  አሸናፊ ድርጅቱ የእህል፣ የባልትና፣ የመድሃኒት እና የማገዶ እንጨት ዉጤቶች ምዕ/ጎ/ዞን ገ/ዉሃ ማረምያ ቤት ንብረት ክፍል በዝርዝሩ መሰረት ማስረከብ አለባቸው፡፡
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ ዋጋ እንዲሁም የማይነበብ ሥርዝ ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ የእህል፣ የባልትና፣ የመድሃኒት እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊ ድርጅት የውል ማ ስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማ ስያዝ በምዕ/ጎን ዐቃቢ ህግ መም ሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  12.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 327 01 63 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ገ/ዉሃ ማረምያ ቤት መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *