Addis Zemen (Jul 10, 2026)
የመጀመሪያ (1ኛ) ዙር የሐራጅ ጨረታ ማስተካከያ
ከባንካችን የተበደሩትን የብድር ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ካልሆኑ ተበዳሪዎች የተረከባቸውን የዋስትና ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በተከራይ የአርባምንጭ ዲስትሪክት በኪዝ ፋይናንሲንግ ሞዳኪቲ ሆፕሻይን ትሬዲንግ የኦክስጂን ማምረቻ ከባንኩ ጋር በገባው የካፒታል ዱቤ ኪራይ ግዥ ውል ስምምነት መሰረት ወቅቱን ጠብቆ የኪራይ ክፍያውን መክፈል ባለመቻሉ ምክንያት ባንኩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በኪራይ ያስተላለፋቸውን የካፒታል እቃዎችን በህጋዊ መንገድ የተረከበ ሲሆን ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በወጣው ማስታወቂያ ማሳሰቢያ ያካተተ በመሆኑ ማሳሰቢያው እንደሚከተለው የተካተተ ሲሆን ሌላው ሰኔ 28 /2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ ፡-
- ከላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች መግዛት የሚፈልግ ተደራዳሪ ተጫራች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25) በመቶ 5,812,500 (አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላሉ።
- ማሽነሪው የተተከለ ሲሆን የሚሸጠው ማሽኑ ብቻ በመሆኑ አሸናፊው ካሸነፈ በኋላ ማሽነሪውን ነቅሎ የመውሰድ ኃፊነት ያለበት ሲሆን የማሽነሪውን መንቀያ እና የትራንስፖርት ወጭ የሚሸፈነው በአሸናፊው ነው::
- የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ስለሆነ ገዥው የቀረጥ ነጻ ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል፤ ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያውን ገዥው ይከፍላል።
- ሐራጁ ነሃሴ 11 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት ይከናወናል።
- ንብረቱን መሉ በሙሉ በካሽ ለሚገዙ ባሸነፉት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያ ጨምሮ አሸናፊው ይከፍላል።
- አሸናፊው የሀራጁ አሸናፊ መሆኑ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ማሽነሪዎችን ለማስጠበቅ የሚከፈል ክፍያ ከማሸነሪዎች መጠለያ ኪራይ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎች የመክፈል ግዴታ አለበት።
- አሸናፊው የባንኩን የኪዝ ፋይናንሲን መስፈርት ካሟላ ሽያጩ በዱቤ ግዥ ይሆናል።
- አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት። ካልከፈለ ባንኩ የሐራጅ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሀራጁ በድጋሚ ይካሄዳል፡፡ በድጋሚ ሲሸጥ የሚፈጠረውን የዋጋ ልዩነት ይከፍላል።
- ሀራጁ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኘበት ነሃሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰአት ንብረቶቹ በሚገኝበት በደ/ኢ/ከ/መ ጋሞ ዞን፣አርባምንጭ ከተማ ይካሄዳል። በሀራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተወዳዳሪ ሀራጁ በሚካሄድበት ቀን የሀራጅ ሰአት ከመድረሱ በፊት ማለትም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሐራጁ ቦታ በመገኘት ምዝገባ ማካሄድ ሲ.ፒ.ኦ እና የታደሰ መታወቂያ ኮፒ ለጨረታው ኮሚቴ ማስረከብ አለበት።
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-181-06-06/03–03 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። ንብረቶቹን በሥራ ሰአት መጐብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ካሉ ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tender.2merkato.com/tenders/6a4b799c0a538aabc5000001