Addis Zemen (Jul 20, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢኳል ኦፖርቹኒቲ አሶሴሽን ፎር ዊሜን ዊዝ ዲስኤቢሊቲስ ሊቪንግ ዊዝ ኤች.አይ.ቪ ሲገለገልበት የነበረውን አንድ ቶዮታ የመስክ መኪና ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች:-
1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤ.ቁ 1057 የኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ ፊት ለፊት በሚገነጠለው አስፋልት እንቁ ስላሴ ጐዳና 70 ሜትር ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3፡00 – ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በአካል ቀርበው ማመልከት ይቻላል።
2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሰርተው ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ሕብረት ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ከ3 የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
4. ተጫራቾች ከድርጅታችን በገዙት የጨረታ ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝ እና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ በፌዴሬሽናችን ጽ/ቤት በመቅረብ በአስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ማስተካከያ ተደረጎ ከጐኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሠነድ ማስገባት ይችላሉ።
6. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘቡን ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዙት ጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጐ ሁለተኛው አሸናፊ ራሱ ባሸነፈበት ዋጋ ከፍሎ እንዲገዛ ይደረጋል።
7. ተጫራቾች የድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ጋር በመቅረብ የንብረቱን ሙሉ መረጃ የያዘ ሠነድ በመግዛት ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በነዚሁ ቀናት በስራ ሰዓት ብቻ መኪናውን በአካል ማየት ይቻላል። ጨረታው በ7ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሠዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
10. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 03 10 25 16 / 09 11 36 21 01/ 09 12 09 46 20
ኢኳል ኦፖርቹኒቲ አሶሴሽን