Reporter (Jul 26, 2026)
በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሀገሬ ብራንድ የሆነውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድኖች ቱታና መለያን ተረክቦ ለሚያከፋፍሉ ንግድ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መስጠት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በፌዴሬሽኑ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በፌዴሬሽኑ ግዥና ፋይናንስ ክፍል በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቴክኒካል ሰነድ በስም በታሽገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ኮፒውን እስከ ሐሙስ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን አሸናፊ የሆነው የትጥቆቹን ሙሉ ክፍያ በመፈፀም በ5 ቀናት ውስጥ መረከብ አለበት።
- ፌዴሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ኢትዮ ቻይና መንገድ
ከቀድሞው አይቤክስ ሆቴል ፊት ስፊት
ስልክ ቁጥር፦ 011 515 8284
አዲስ አበባ