ግሎሪየስ ኃላ/የተ/የግል/ ኩባንያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ግሎሪየስ ኃላ/የተ/የግል/ ኩባንያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Jul 26, 2026)

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጹት መስፈርቶች መሰረት እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

የጨረታ ሁኔታዎች

1. ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ቃሊቲ በሚገኙት እና ሌሎች የድርጅቱ መጋዘኖች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ተሽከርካሪዎችን መመልከት ይችላሉ እንዲሁም ለአስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጨረታ ዋጋቸውን ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ በታሽገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይችላሉ።

2. ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ለጨረታ ማስረከቢያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ (CPO) ለሚወዳደርበት ተሽከርካሪዎች 5/100 (አምስት በመቶ) ማስያዝ አለባቸው።

3. በጨረታ አሸንፈው ከፍለው ተሽከርካሪዎችን ለማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

4. የጨረታው አሸናፊ ከተሽከርካሪዎች ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ የሚታሰብ ግብር፣ ከስም ማዘዋወርያ ክፍያ ጋር የተገናኙ ወጪዎች ፣እና ሌሎች በህግ የተወሰኑ ወጪዎች የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል።

5. ጨረታው ሀምሌ 30 ቀን 2018 . 10:45 ሰዓት ተዘግቶ በነሃሴ 1 ቀን ከሰአት 8 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና ቢሮ ይከፈታል።

6. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ዋጋ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ በመክፈል ተሽከርካሪውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው::በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ተሸከርካሪውን የማይረከብ ተጫራች የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

7. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለጸ በኃላ ያስያዙት ../ bank guarantee/ ይመለስላቸዋል።

8 ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

ድርጅት ግሎሪየስ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ

ሱማሌ ተራ ግሎባል ሕንፃ

6ተኛ ፎቅ (ስልክ፡– 011 1 57 66 93)

ማሳሰቢያ፦ ተሽከርካሪዎቹባሉበት ሁኔታ እና ቦታ ይሰጣሱ፤ ተሽከርካሪውን ማንሳትና ማጓጓዝ የጨረታው አሸናፊ ኃላፊነት ነው::-


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *