በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ዉስጥ የሚገኘው የወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ዉስጥ የሚገኘው የወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር፦ አዲስ/ክ/ከ/ወ/6/004/2018

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ክልል ዉስጥ የሚገኘው የወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 01 የደንብ ልብስ = 11,000.00 ብር
  • ሎት 02 የፅዳት ዕቃዎች = 14,000.00 ብር
  • ሎት 03 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች = 14,000.00ብር
  • ሎት 04 የህትመት = 5,000.00ብር
  • ሎት 05 ትራንስፖርት = 3,000.00 ብር
  • ሎት 06 መስተንግዶ = 23,000.00 ብር
  • ሎት 07 የደብ ልብስ ስፌት = 3,000.00 ብር
  • ሎት 08 የቢሮ እቃዎችና ኤሌክትሮኒክስ ጥገና = 5,0000.00ብር
  • ሎት 09 ዲኮርና ሞንታርቦ ኪራይ = 3,000.00ብር
  • ሎት 10 የጭነት አገልግሎት = 3,000.00ብር
  • ሎት 11 የመኪና ጎማ እቃዎች = 23,000.00ብር
  • ሎት 12 የጉልበት ሠራተኛ…….

ተጫራቾች ከሚጫረቱበት እቃ ጋር ግንኙነት ያለዉ የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ በጨረታዉ ተካፋይ መሆን እንደሚችሉ የሚያመለክት ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ያቅራቢ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት ከሚጫረታቸዉ ሰነዶች ጋር አባሪ መሆንይኖርበታል።

የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 402 ከ2ኛ ፎቅ ላይ ፋይናንስ ፅ/ቤት በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ለፋይናንስ ፅ/ቤት ማስያዝ ይኖርበታል።

2. የጨረታው ሰነድ ሲገባ ናሙና አብሮ መቅረብ አለበት፤ ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡበት ሰነድ ዋናዉና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገት አለባቸው።

3. ጨረታውን ያሸነፈዉ ተጫራች ከመስሪያ ቤታችን ጋር ውል ተዋዉሎ የዉል ማስከበሪያ ዋጋውን 10% ዋጋ መስያዝ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪ የአሸናፊውን እቃ በ10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ባይሆን ግን ለጨረታዉ የተያዘዉን ቼክ ዋጋ በቀጥታ ገቢ ሆኖ ከጨረታዉ ይሰረዛል።

4. ጨረታዉ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት ይዘጋል ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰአት ይከፈታል።

5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነዉ።

6. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አካላት በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ብቻ መወዳደር ከፈለጉ የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅሶ ህጋዊ ዋስትና ማስረጃ ሲያቀርቡ ሰነድ ወስደው መወዳደር ይችላሉ።

7. በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑይመለሰላቸዋል።

8. ጽ/ቤቱ ከውል በፊት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ ከውል በኋላ 25% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው

9. አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

10. አሸናፊዉ ያሸነፈባቸዉን ንብረቶች የወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራጮች የአንዱ ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

12. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚያስገባው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።

አድራሻ ፡- ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ጨው በረንዳ በሚወስደው መንገድ ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 200 ሜትር ርቀት ላይ ወረዳ 6 አስተዳደር ገቢ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ውስጥ መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011-2-73-58-85 ወይም 0112 -77-48-00

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት