ፀደይ ባንክ አ.ማ. ስፋቱ 240 ካ.ሜ. የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በግልጽ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፀደይ ባንክ አ.ማ. ስፋቱ 240 ካ.ሜ. የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በግልጽ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Aug 12, 2026)

ፀደይ ባንክ አማ /ማርቆስ ዲስትሪክት

የሀራጅ ጨረቃ ማስታወቂያ

ጸደይ ባንክ አ.ማ. ለአቶ  ማረልኝ ባለው የሰጠው ብድር ባለመመለሱ ባንኩ በዋስትና /በመያዣ/ የያዘው በሞጣ ከተማ ቀበሌ 05 በካርታ ቁጥር  3374/2012 ተመዝግቦ የሚገኝ  ስፋቱ 240 ካ/ሜ የሆነ  የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በጸደይ ባንክ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. የቤቱ ጨረታ መነሻ ዋጋው ብር 400,723.88  / አራት መቶ ሰባት መቶ ሃያ ሶስት ብር ከሰማኒያ ስምንት ሳንቲም / ነው
  3. በጨረታ የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።
  4. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።
  5. የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪውን ገንዘብ 15 ቀን ውስጥ ለባንኩ በመክፈል ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በዚህ ቀን ውስጥ ካልከፈለ ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ¼ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  6. በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ይመለስላቸዋል።
  7. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያየዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላሉ። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  8. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
  9. ጨረታው የሚካሄደው በሞጣ ከተማ ቀበሌ 05 ለጨረታ በወጣው ንብረት ግቢ ውስጥ ነው።
  10. ጨረታው የሚካሄደው መስከረም 10 ቀን 2019 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት ይሆናል።
  11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  12. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 21 66 71 15/ 09 12 43 68 68 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

ስልክ  058 771 2034

ፖ.ስ.ታ  341   

ፋክስ  058 771 6667

ቁጠባችን ለነገ ዋስትናችን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *