Addis Zemen (Aug 13, 2026)
የግልፅ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
1ኛ ዙር መለያ ቁጥር 001/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ወረገኑ ቅደመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሎት ዝርዝር ይሆናሉ።
|
ተ.ቁ |
የሎት ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ ብር |
|
1 |
የደንብ ልብስ |
20,000 |
|
2 |
የስፖርት ትጥቅ |
20,000 |
|
3 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
40,000 |
|
4 |
አላቂ የፅዳት ዕቃዎች |
40,000 |
|
5 |
የሕንፃ ቁሳቁስ መግዣ |
60,000 |
|
6 |
የኤሌክትሮኒክስ መግዣ |
65,000 |
|
7 |
የትምህርት ዕቃዎች |
30,000 |
|
8 |
የሕክምና ዕቃዎች |
10,000 |
|
9 |
ሕትመት |
10,000 |
|
10 |
ልዩ ልዩ መሣሪያዎች |
10,000 |
|
11 |
የኤሌክትሮኒክስ ጥገና |
10,000 |
|
12 |
የሕንፃ ቁሳቁስ ጥገና |
10,000 |
|
13 |
የጭነት አገልግሎት |
10,000 |
|
14 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
10,000 |
|
15 |
ምንስትርምንግ /ልዩ ልዩ |
10,000 |
ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳዲሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በገንዘብና በኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
3. የ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
5. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር /200.00/ ሁለት መቶ ብር በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር (3) እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።
6. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር (3) ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበት የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል። በቀጣይ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ የተጠቀሰውን ብር ከባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። የማይቀረብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
10.የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ 10% ከባንክ የተረጋገጠ /CPO/ማስያዝ ይኖርበታል።
11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ወረገኑ ቅደመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል።
12. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ስልክ ቁጥር 011 866 9955/ 09 24 26 44 27 ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈጬ የሚወስድ መንገድ ወደ ቀኝ 3 ከሎ ሜትር ላይ ይገኛል።
ቦሌ ወረገኑ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት