Addis Zemen (Aug 13, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ 001
በአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት አመት በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ባወጣው ግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች የተዘጋጀ አገልግሎት ግዥ
- lot 1 የእስቴሽነሪ መሳሪያዎች፣
- lot 2 የፅዳት እቃዎች፣
- lot 3 ደንብ ልብስ፣
- lot 4 ኤሌክትሮኒክስ፣
- lot 5 ህትመት፣
- lot 6 መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች፣
- lot 7 ቋሚ እቃዎች አወዳድሮ በጨረታ ለመግዛት እና
- lot 8 የሽንት ቤት ቆሻሻ መጸዳጃ አገልግሎት ለማስወገድ ለአንድ አመት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በመስኩ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ እና በዌብሳይት የሚረጋገጥ
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ሰርተፍኬት ወይም ፐOT 3%
5. በመድሀኒት ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር 4 ባለስልጣን ላይሰንስ ሊኖር ይገባል።
6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ
- lot 1 የእስቴሽነሪ መሳሪያዎች 2%(5000)፣
- lot2 የፅዳት እቃዎች 2%(5000)፣
- lot3 ደንብ ልብስ 2%(5000)፣
- lot4 ኤሌክትሮኒክስ 2%(3000)፣
- lot 5 ህትመት (5000)፣
- lot6 መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች 2%(10000)፣
- lot7 ቋሚ እቃዎች 2%(10000) አወዳድሮ በጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል እና
- lot 8 የሽንት ቤት ቆሻሻ መጸዳጃ አገልግሎት 2%(2000) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር ጉዳዮች እና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ 1 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
8. ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11፡30 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚዘጋው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ታሽጎ 3፡00 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. አሸናፊው ድርጅት ውል በተፈራረሙበት በ5 ቀን ውስጥ እቃውን ያቀርባል።
10. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት በአካል በመቅረብ ስራውን ማከናወን አለበት።
11 ጨረታው ከተከፈተ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
12. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጫረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው እና በእያንዳንዱ ላይ ገጽ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
13. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብም ሆነ ድርጅት ውል በሚያዝበት ወቅት ያሸነፈበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማሸከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (cpo) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
14. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ 15% vat ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ ይኖርበታል ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
15. ኦርጅናል ሰነድ ከሙሉ ሰነድ ጋር እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ ተደርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የድርጅቱ ማህተብ እያንዳንዱ ሰነዶች ላይ መደረግ አለበት።
16. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
17. ማንኛውም ተጫራች መደበኛ የጨረታ ሰነዱን የሚሞሉ ክፍሎችን በአግባቡ ሞልቶ ተመላሽ ያላደረገ አቅራቢ ቅድመ ምርመራ ጨረታ ላይ ውድቅ ይደረጋል።
18. የጥቃቅን አነስተኛ የተደራጀ ልዩ አስተያየት የሚደረገው በሚያመርቱት ምርት ብቻ ሆኖ ከተደራጁበት ተቋም በሚያቀርቡት ደብዳቤ ይሆናል።
ተጨማሪ መረጃ፡- የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ አ/ከ/ክ/ከ/ጤና ጣቢያ መሳለሚያ እህል በረንዳ ከእሳት አደጋ በስተጀርባ በሚገኘው ግዥ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0112756204 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ