Addis Zemen (Aug 18, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን፣ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣የደንብ ልብሶችን፣ የፅዳት እቃዎችን፣ ቋሚ እቃዎች ግዥ፣ ህትመትና መፃሐፍቶችን፣ የመኪና ኪራይ፣ የጉልበት አገልግሎት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ እንዲሁም የመስተንግዶ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለእያንዳንዱ ማስያዝ የሚገባቸው የጨረታ ማስከበሪያ
1. ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ 50,000
2. ሎት 2. የደንብ ልብስ ግዥናስፌት 50,000
3. ሎት 3 የፅዳት እቃዎች 50,000
4. ሎት 4 የተለያዩ ህትመትና የህክምና መፃሕፍቶች 50,000
5. ሎት 5 ቋሚ እቃዎች ግዥ 100,000
6. ሎት 6 የመኪና ኪራይ አገልግሎት 50,000
7. ሎት 7 የጉልበት አገልግሎት 50,000
8. ሎት 8 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ 100,000
9. ሎት 9 የመስተንግዶ አገልግሎት 50,000
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ በፌዴራል ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ የምስክር ወረቀት ያለው።
2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸውና የግብር ከፋይ ቲንና የምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በአንድ ሎት 500 ብር (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ አጃምባ ኮንዲሚኒየም ከነማ የህዝብ መድሃኒት መሸጫ አጠገብ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 64 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10(አስር) የስራ ቀናት እስከ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት (አስራ አንድ ሰዓት) ድረስ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ቢሮ ቁጥር በመምጣት መግዛት ይቻላል።
5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ናሙና ወይም ሳምፕል ለማቅረብ የማይመቹ እቃዎችን በአካል ማሳየት የሚችል።
6. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም።
7. ገዥው በአካል የሚገዛውን እቃ አስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በየሎቱ ለየብቻ በኢንቨሎፕ በማሸግና ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ዋጋ ከዚህ በላይ የቀረበውን ዝርዝር በማየት በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ እንዳለባቸውና ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ቁጥር 64 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ወይም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. አሸናፊው ከታወቀ በኃላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም ከ7ቀን በኋላ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው።
11. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ቢሮ ቁጥር 48 አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
12. መስሪያ ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ድርጅቶች ከሚመለከተው አካል በኃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡– ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ አጃምባ ኮንዲሚኒየም ከነማ የህዝብ መድሃኒት ቤት አጠገብ ላይ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ፡– ስልክ ቁጥር፡ 09 20 09 03 56 መጠየቅ ይችላሉ።
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ