Addis Zemen (Aug 21, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት/001/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል ፡፡
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለማሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1.ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2.በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3.የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
4.ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5.ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ.ብር |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ |
17,000(አስራ ሰባት ሺ ብር)ብቻ |
|
ሎት 2 |
አላቂ የቢሮ እቃዎች |
10,000(አስራ ሺ ብር)ብቻ |
|
ሎት 3 |
ህትመት |
1,500(አንድ ሺ አምስት መቶ ብር)ብቻ |
|
ሎት 4 |
አላቂ የትምህርት እቃዎች |
20,000(ሀያ ሺ ብር )ብቻ |
|
ሎት 5 |
አላቂ የጽዳት እቃዎች |
10,000(አስር ሺ ብር) ብቻ |
|
ሎት 6 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
3,000(ሶስት ሺ ብር) ብቻ |
|
ሎት 7 |
የኤሌክትሮኒክስ ማሽነሪ እድሳት ና ጥገና |
8,000(ስምንት ሺ ብር) ብቻ |
|
ሎት 8 |
የትራንስፖረት መኪና የጭነት |
5000(አምስት ሺ ብር ብቻ) |
|
ሎት 9 |
የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ እቃዎች |
40,000(አርባ ሺ ብር )ብቻ |
|
ሎት 10 |
ተገጣጣሚ የፈርኒቸር እቃዎች |
23,000(ሀያ ሶስት ሺ ብር )ብቻ |
6.የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
7.ተጫራቾች በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በራሳቸው ምርት ብቻ ካደራጃቸው ጽ/ቤት የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ደብደቤ በማፃፍ መወዳደር ይችላሉ፡፡ የራሳቸው ምርት ካልሆነና ገዝተው ለሚያቀርቡት እቃ የጨረታ ሰነድ መግዥያና የጨረታ ማስረከቢያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8.ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10(አስር)ተከታታይ የስራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
9.ጨረታው በአስረኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
10.ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
11.ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
12.የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
13.መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና የትራንስፖርት መኪና/የጭነት መኪና አሸናፊው ለአንድ አመት ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
15. የጨረታ ሰነዱን በትክክል በማንበብና በመሙላት ማህተምና ፊርማ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ በማድረግ ዋጋ መሙያ ሎቱን ብቻ ቀዶ በማውጣት መሙላት ከጨረታው ውድቅ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ የጨረታ ሰነዱ ሁሉም በስርዓት በመሞላት ገቢ መሆን አለበት፡፡
16. ዋጋው ከነቫቱ መሞላት ይኖርበታል፡፡
17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ ነው፡፡
አድራሻ ፡– ከቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ዝቅ ብሎ
በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ኦዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት