በጅማ ዞን የኦሞ ቤየም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በጅማ ዞን የኦሞ ቤየም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 21, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በጅማ ዞን የኦሞ ቤየም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • የፅሕፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክንስ ኢቃዎች፣
  • ቋሚ የቢሮ እቃዎች (office furniture) የተለያዩ የተሽከርካሪና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፤
  •  የቧንቧ እና የህንፃ መሳሪያዎች ለቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም የሚውሉ መሳሪያዎች፤
  • የተለያዩ ሞዴል ሞተር ሳይከሎች፤ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፤ የደረቅ ዕቃዎች ማጓጓዣ ትራንስፖርት አገልግሎት፤
  • የተለያዩ ተሽከሪካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች የመለዋወጫና ጥገና አግልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፦

1. በንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የ2019 ዓ.ም የዘመኑን ግብር ከፍሎ ንግድ ፈቃዱን ያደሰና ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡

2. በንግድ ዘርፍ በአቅራቢያዎች ዝርዝር መዝገብ ላይ የተመዘገበና መረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3. የግብር ክፍዮች መለያ ቁጥር TIN-NO ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

5. ለእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ (የውድድር ዓይነት) የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡

6. በጥቃቅንና አነስተኛ (በማይክሮ) የተደራጁ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተወዳድሮ ያሸነፈዉን እቃ ሁሉ እስከ ኦሞ ቤየም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት ንብረት ክፍል (ዳሎታ ከተማ) በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ አቅርቦ ንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

8. በዚህ ጨረታ ላይ መወዳደር የሚችል የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ እንዳይወዳደር ያልተከለከለ ወይም የተከለከለ ከሆነ የጊዜ ገደቡን የጨረሰ መሆን ይኖርበታል፡፡

9. የራሱ ባልሆነ ንግድ ፈቃድ የሚወዳደር ማንኛውም ተወዳዳሪ በሌላ ሰው የንግድ ፈቃድ ውክልና አለኝ በማለት መወዳደር አይችልም፡፡

10. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 ድረስ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ኦርጅናልና ኮፒ Copy በı (አንድ) ፖስታ ውስጥ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

11. ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ፈርማውንና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

12 የቢሮ ውስጥ ዕቃዎችን (office furniture) ለማቅረብ የሚወዳደር ተወዳድሮ ያሸነፈውን ዕቃዎች ገጥመው ማስረከብ ይኖባቸዋል፡፡

13. ለዚህ የተዘጋጀ ጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከኦሞ ቤየም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡

14. የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 21 የሥራ ቀን (ሃያ አንድ) የሥራ ቀን ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡

15. ጨረታው በ22 ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ውኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡

16. የ22ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

17. መ/ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ በስተደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ ከተማ በሚወስደው ዋናው የአስፓልት መንገድ ከአ/አበባ ዳሎታ ከተማ 326 ኪ/ሜትር፤ከጅማ ከተማ ዳሎታ ከተማ 93 ኪ/ ሜትር ርቀት ላይ እንገኛለን፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 17 10 78 79 ወይም 0917 00 17 18 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በጅማ ዞን የኦሞ ቤየም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት