Addis Zemen (Aug 28, 2026)
1ኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፣ አ/ከ/ክ/ከ/ወ/5/ፋ/ጽ/001/19
በአ/ከ/ክ/ ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
ከጠቅላል ዋጋ የሚያሲዙት/የብር መጠን/ |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
27,234.85 |
|
ሎት 2 |
ቋሚ ዕቃዎች |
5,000.00 |
|
ሎት 3 |
የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች |
15,448.42 |
|
ሎት 4 |
የፅዳት ዕቃዎች |
18,469.14 |
|
ሎት 5 |
የቢሮ መስተንግዶ |
22,648.8 |
|
ሎት 6 |
የመኪና ኪራይ |
14,593.59 |
|
ሎት 7 |
የተለያዩ የዲኮር ስራዎች |
5,003.75 |
|
ሎት 8 |
የጉልበት ሰራተኛ |
5,250.00 |
|
ሎት 9 |
የሕትመት ስራዎች |
1000.00 |
|
ሎት 10 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
10,000.00 |
|
ሎት 11 |
የተለያዩ የግብርና ዘሮች |
4,500.00 |
|
ሎት 12 |
የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ |
22,648.8 |
በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
- የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው።
- የቫት/TIN NO/ ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር በዌብ ላይት ስለመመዝገባቸው መረጃ የምናይ መሆኑን
- ተጫራቾች ለመወዳደር የጨረታ ሰነድ ስታስገቡ ለተወዳደራችሁበት አላቂ ዕቃ እና የልብስ ስፌት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /cpo/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5% በማስላት በማስያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይህን ካላቀረቡ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በማይመለስ ብር በካሽ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል በወረዳ 5 ፋ/ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ወደ ቢሮው ሲገቡ በስተቀኝ በመግባት መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሠነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸው ከፍሎች በሙሉ መሞላት አለባቸው።
- በስራ ኢንተርፕራይዝ የተደረጃችሁ በራሳችሁ ምርት ላይ ልዩ አስተያየት ስለሚደረግ አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ ካደራጃችሁ አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።
- በስራ ኢንተር ፕራይዝ የተደራጃችሁ ከምታመርቱት ምርት ውጪ ባለ ዘርፍ እና ሰነድ ላይ እንደማንኛውም ተጫራች ድርጅት cpo ማስያዝ ይኖርባችኋል።
- ለሰራተኞች ካፍቴርያ መብራት ክፍያ በወር 4,000 ውሃ የቤት ኪራይ ‘የመስሪያ ቁሳቁሶች ከመ/ቤቱ የሚቀርብ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን አካተው ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሱን ማግለል አይቻልም።
- የተጫራቾችን አድራሻ የሚገልፅ ሙሉ መረጃ ከሰነዱ ጋር መያያዝ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ካሽነፈው ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንከ የተረጋገጠ /cpo/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የቢሮ መስተንግዶ ላይ የምትወዳደሩ የውሃና የቆሎ ሳምፕል ማቅረብ አለባችሁ። ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ድርጅት ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች ድርጅት የአሸነፋችሁትን ዕቃ በራሳችሁ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ማቅረብ አለባችሁ።
አድራሻ፡- ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጳውሎስ ቅርንጫፍ ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም መውረጃ 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡።
ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 011-230-6998 / 09 27 60 26 30/
ማሳሰቢያ፡-
- በተጫረታችሁበት ዕቃ ላይ ዋጋ ስታስገቡ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅብዎታል መወዳደር የሚቻለው ንግድ ፍቃዱ ላይ በተሰጠው ስራ ዘርፍ ብቻ ነው።
- ተጫራቾች ያስገባችሁትን ሳምፕል በቂ ማስቀመጫ ቦታ ስለሌለን አሸናፊና ተሸናፊ ከተለየ በኋላ በ60 ስልሳ የስራ ቀናት ውስጥ እንድትወስዱ እያሳሰብን በተቀመጠው ቀናቶች ውስጥ የማይወስድ ተጫራች ጽ/ቤቱ መስሪያ ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዛችሁትን cpo ለውል ማስከበሪያ ማዞር ማስያዝ አይቻልም።
- ተጫራቾች ዋና የጨረታ ሰነድ ላይ ክፍል 2/ሁለት/ እና ክፍል 6/ስድስት/ በተጫራቾች የሚሞላውን ቅጽ መሙላት እና በየአንድአንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መመለስ ይኖርባችኋል። ነገር ግን ከፍል 2 እና ክፍል 6 ላይ በተጫራቾች የሚሞላውን ቅፅ ያልሞላ ተጫራች እና
- የጨረታ ሰነዱን ካልመለሰ /ተመላሽ ካላደረገ ከላይ የተጠቀሱትን ያላሟላ ተጫራች ጨረታው ውድቅ ይሆንበታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያም ሆነ ለውል ማስከበሪያ የምታሲዙት በCPO ብቻ ነው። ከሲፒኦ ውጪ በቼክና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም። ካስያዛችሁም ከውድድር ውጪ ትሆናላችሁ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት