Addis Zemen (Aug 28, 2026)
ሁለተኛ ዙር የሀራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማትባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት ከአቶ ብሩህ ተስፋ ጥሩነህ ባልተከፈለ ዕዳ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና 807/2005 መሰረት የተረከባቸውንና ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን ለቡና መቁላት፣ መፍጨትና ማሸግ ስራ የሚያገለግሉና ጣሊያን ስሪት የሆኑ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ. |
የንብረቱ ዝርዝር |
ብዛት በቁጥር |
የሐራጁ መነሻ ዋጋ |
የንብረቱ ሁኔታ |
ሐረጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
Coffee Roasting and Grinding Machinery |
|
84,205,883.24 |
አዲስ |
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
|
1.1 |
Pneumatic Loader Model ELP60 |
1 |
|||
|
1.2 |
Coffee Roaster Model – TTG 60 |
1 |
|||
|
1.3 |
Roasted Coffee Receiving Hopper |
1 |
|||
|
1.4 |
Loader (Pneumatic Conveyor system |
1 |
|||
|
1.5 |
Suction Pump group for Pneumatic conveyor system |
1 |
|||
|
1.6 |
Silos for roasted coffee beans |
2 |
|||
|
1.7 |
Drop diverter valve |
2 |
|||
|
1.8 |
Additional Unit of Pneumatic conveyor to feed the roasted coffee beans to packing machine |
1 |
|||
|
1.9 |
Coffee Grinder Model-MAIN 300 |
1 |
|||
|
1.10 |
Raking Screw Conveyor to feed the ground coffee to silo |
1 |
|||
|
1.11 |
Ground Coffee Silo |
1 |
|||
|
1.12 |
Electric Control Panel Molim |
1 |
|||
|
2. |
Auto Weighing and Vertical Packaging Machinery Brand: DOLZAN, Model: D150-C1, Origin: Italy, Manu facturing Year: 2021 |
1 |
የሀራጁ መመሪያ:
- ንብረቱን መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የሀራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር 16,841,176.65/አስራ ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አንድ ሺ አንድ መቶ ሰባ ስድስት ብር ከ65/100 ሳንቲም/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማቅረብ በሀራጁ መሳተፍ ይችላል። ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ከንብረቱ የመሸጫ ዋጋ ላይ |ተጫራቹ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ/ የሚቀነስ ይሆናል።
- ንብረቱ በሲዳማብ/ክ/መንግስት ይርጋዓለም ከተማ፣ ይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚገኘው ሺድ ውስጥ ይገኛል።
- የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ ግን የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።
- ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ በካሽ/ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥው በሕግ እንዲከፍላቸው የተወሰነ የታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
- የሐራጁ አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። የሀራጁ አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ በድጋሚ ይካሄዳል። ለተሸነፉ ተጫራቾች ለሀራጁ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያወኑ ይመለስላቸዋል።
- ተጫራቹ በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን የማሽነሪኪራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ቀሪ ክፍያ አጠቃሎ በመክፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
- የካፒታል ዕቃውን ካለበት መጋዘን ወደ ሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣ የመትከያ፣ ስራ የማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ተከራይ ይሸፍናል።
- ሀራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ይካሄዳል።
- ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
- ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሀራጁ አይገደድም።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት