Addis Zemen (Sep 01, 2026)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ዋና ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ለሚገኙ ለ12ቱ መምሪያዎች በ2019ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን
- ሎት 1. የፅህፈት እቃዎች
- ሎት 2. የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣
- ሎት 4. አልባሳት፤
- ሎት 5.የህንፃ መሳሪያ
- ሎት 6 ህትመት
- ሎት 7. የመኪና ጎማ፣
- ሎት 8.የእስረኛ ቀለብ፣
- ሎት 9 መኪና ኪራይ
- ሎት 10. መድኃኒቶች
- ሎት 11 ቋሚ እቃ እና
- 12ኛ የካምፕ መመግቢያ እቃዎች እና
- ሎት 13. ጉልበት ሰራተኛ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል በዚህም መሰረት፡-
1. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆነው በስራ መስኩ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ለሎት 1፣ 2 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 3፣8 ና 13 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ ሎት 4፣6፣7 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 5 ና 9 4,000 /አራት ሺህ ብር/ ሎት 10 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 11 እና 12 6,000 /ስድስት ሺህ ብቻ /ሲፒኦ /CPO/ በመ/ቤታችን ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. በሎት የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ቴሌ ብር በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 503 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቸላሉ ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጨረታው ለመወዳደር
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ስነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ዋና ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 503 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ጨረታውን ሲወዳደሩ በእያንዳንዱ ከላይ በተ.ቁ 1 ላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች አሟልቶና አያይዞ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
5. ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በክ/ከተማው የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
6.ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ዕቃ ላይ መ/ቤቱ መመዘኛ መስፈርት/Specification/ባወጣንባቸው ዕቃዎች ላይ ሌላ የራስን መመዘኛ /Spec/ አውጥቶ መወዳደር አይቻልም፡፡
7.ተጫራቾት የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
8.የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ በጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. የጨረታው አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ 10% ዋስትና መስጠት ይኖርበታል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-
ን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በስልክ ቁጥር፡-
0114423315/0114431529/ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ