Addis Zemen (Aug 31, 2026)
የግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 11 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ጥራታቸውን የጠበቁ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማ የጭነትአገልግሎት እና የትራንሰፖርት አገልግሎት፣ መስተንግዶ፣ ህትመት፣ ዲኮር ኪራይና ድንኳን ኪራይ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የቢሮ ፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ቦ/ክ/ወ/11/ፋ/ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው
6. ህጋዊ መንጃ ፍቃድ ያላቸው ለጭነትና ለትራንስፖርት
7. የባለቤትነት መታወቂያ ድብተር/ሊብሬ| ያለው /ለጭነትና ለትራንስፖርት
8. ሶስተኛ ወገን /ኢንሹራንስ⁄ ያለው ለጭነትና ለትራንስፖርት
|
ሎት ቁጥር |
ሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስረከቢያ በበኢትዮ ብር |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ
|
5000.00/አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 2 |
አላቂ ጽህፈት መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
|
10,000 /አስር ሺህ ብር/ |
|
ሎት 3 |
አላቂ የጽዳት እቃዎች
|
5000.00/ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 4 |
የመስተንግዶ አገልግሎት
|
5000 / አምስት ሺህ ብር/
|
|
ሎት 5 |
የህትመት አገልግሎት
|
5000.00 /አምስት ሺህ ብር/
|
|
ሎት 6 |
የዲኮርና ድንኳን ኪራይ አገልግሎት
|
8000.00/ ስምንት ሺህ ብር/
|
|
ሎት 7 |
ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
|
2500.00 /ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር/
|
|
ሎት 8 |
ፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት
|
2500.00/ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር/
|
|
ሎት 9 |
የመኪና ጎማ
|
10,500/አስር ሺህ አምስት መቶ ብር/
|
|
ሎት 10 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
5000/አምስት ሺህ ብር/
|
|
ሎት 11 |
የጭነት አገልግሎት |
5000/አምስት ሺህ ብር/
|
|
ሎት 12 |
የልብስ ስፌት
|
2500.00/ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/
|
|
ሎት 13 |
ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ |
20,000/ሃያ ሺህ ብር/
|
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 004 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን የእቃ ዓይነቶች ውል ከፈረሙበት ጊዜ ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ አጠናቀው ገቢ ማድረግ አለባቸው። በተቀመጠው ቀነገደብ ያላስገቡ ተጫራቾች በህግ የሚጠየቁ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ወረዳ 11 ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 011 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋው ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋናውን የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው
6. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
7. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
8, መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. የጥቃቅን አነስተኛ ተጫራች ባመረቱት ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ። ነገር ግን ባላመረቱት ምርት ከሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ገዝተው እንዲሁም ሲፒኦ አስይዘው መወዳደር ይችላሉ።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፤- ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር አደባባዩን ወረድ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-8931-1119
በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 11 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት