Addis Zemen (Sep 02, 2026)
የድርድር የሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰውን የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ክራይ ተከራይ በውሉ መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በድርድር ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ አልያም የባንኩን መስፈርት ለሚያሟሉ መልሶ ማከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የካፒታል ዕቃው የቀድሞ ተከራይ ስም |
የካፒታል ዕቃው ዓይነት |
ካፒታል ዕቃው የሚገኝበት ቦታ |
የድርድሩ መነሻ ዋጋ (ብር) |
ድርድሩ የሚካሄድበት ቦታ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
ኤክሶደስ ኬሚካል አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር |
የዶሎማይት ማምረቻ ማሸን እና አንድ ዋል ሎደር |
ቢሾፍቱ ከተማ፤ በተከራዩ የማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
64,093,679.68
|
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዲስትሪክቱ ጽ/ቤት ውስጥ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4፡00 ጀምሮ |
ማሳሰቢያ፡–
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መደራደር ይችላሉ።
- ተደራዳሪዎች የድርድር ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት በመውሰድ ከፒታል ዕቃውን የሚገዙበት ዋጋ፤ የክፍያው ዓይነት በካሸ ወይም በዱቤ ግዥ)፣ ዱቤ ከሆነ ቅድመ ክፍያ እና ቀሪው የሚከፈልበት የመክፍያ ጊዜ በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም ከጧቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሸያጭ ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል።
- ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጀቶች በመወከል በሸያጭ ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውከልና ስልጣን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሸ ይደረጋል።
- በጥሬ ገንዘብ ያሸነፈው ተጫራች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል ይገደዳል::
- በጥሬ ገንዘብ ያሸነፈው ተጫራች 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛዋወሪያ ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
- አሸናፊ ተጫራች ማሸኑን ካለበት ማምረቻ ቦታ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡– 022-211-66 87 ላይ መደወል ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ
- ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አሰቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ድርድሩን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት