Addis Zemen (Sep 12, 2026)
የሐራጅ ማስታወቂያ
የሐራጅ መለያ ቁጥር 01/2018
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ የተለያዩ ማሽነሪዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተጫራች ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት መሳትፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ኩባንያው የተለያዩ 80 ማሽነሪዎች በሐራጅ የሚሸጥ ሲሆን የማሽኖቹን ዝርዝር ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የሐራጅ ሽያጭ ሰነድ ላይ የሚያገኙ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያም የሚወዳደሩበትን የማሽን አይነቶች ጠቅላላ የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባችኋል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ማሽኖቹን ኩባንያው በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት በአካል ተገኝተው ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው በመቅረብ ከጨረታው ቀን በፊት መጎብኘት ይኖርባቸዋል፡፡
- በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመካሄዱ ከጠዋቱ 4፡30 በፊት ባለው ጊዜ ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል በኩል ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል። ሐራጁ በቀን 19/1/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው የኩባንያው መጋዘን የሚካሄድ የሆናል።
- ሐራጁ ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት በኩባንያው መጋዘን ውስጥ ይካሄዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ አስ⁄ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ 200 ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የሐራጅ ጨረታው ከተካሄደበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ለኩባንያው አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ክፍያውን በፈጸመ በ10 ቀናት ውስጥ ማሽኖቹን ማንሳት አለበት፡፡
አድረሻ፡- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተሻግሮ የ6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን በሚገኘው የኩባንያው ህንፃ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-2-179967 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ