Addis Zemen (Sep 13, 2026)
የግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019ዓ.ም
የካራአሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።
|
ሎት 1 |
ደንብ ልብስ የመምህራን ጋዋን የስፖርት ቱታና የስፖርት ጫማ በአገር ውስጥ የተሰራ የመሳሰሉት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1፤25,000.00ብር |
|
ሎት 2 |
አላቂ የቢሮ እቃ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 2፤15,000.00ብር |
|
ሎት 3 |
ህትመት (መታወቂያ ካርድ) እና የመሳሰሉት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት3 5,000.00 ብር |
|
ሎት 4 |
አላቂ የህክምና እቃዎች እና የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ እና ሌሎችም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 4፤5000.00 ብር |
|
ሎት 5 |
አላቂ የትምህርት እቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 5፤20,000.00 ብር |
|
ሎት 6 |
ሌሎች አላቂ እቃዎች |የጽዳት እቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 6 ብር፤15,000.00 |
|
ሎት 7 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች የቢሮ መገልገያ እቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 7፣ 8000.00 |
|
ሎት 8 |
ቋሚ የቢሮ እቃ (ፕላንትና ማሽነሪ )ግዢ ለምሳሌ፤ ኮምፒዩተር፤ ፕሪንተር እና ላብቶፕ የመሳሰሉት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 8፤40,000.00 ብር |
|
ሎት 9 |
ውሃ፤ ቆሎ፤ ኩኪስ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 19፤ 5000.00 ብር |
|
ሎት 10 |
ቋሚ ዕቃ መግዣ(ለምሳሌ ተሸከርካሪ ወንበር የተለያዩ ፈርኒቸሮች እና የመምህራን ማረፊያ ጠረጴዛ የመሳሰሉት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 10፤25,000.00 ብር |
|
ሎት 11 |
ሎት 11 የመጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 11፤5,000.00 ብር |
በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ።
በመስኩ ወይም በሙያው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ አቅራቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችል፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የምታቀርቡበት ሰነድ ኮፒ ለእይታ የማያስቸግር ግልጽ መሆን ይኖርበታል።
ከገቢዎች የሚሰጥ ክሊራንስ እና ዋጋውን ሞልታችሁ የምታስገቡት ሰነድ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ።
- የንግድ ስራ ፈቃድ መስክ ጀርባ ይመልከቱ የሚለውን ኮፒ ጨምሮ ማቅረብ
2. ህጋዊ የካሽ ሬጅስተር ማሽን ደረሰኝ ወይም መብራት ሲጠፋና ማሽኑ ለጥገና ሲገባ የገባበት ደብዳቤ እና ህጋዊ የገቢዎች ፍቃድ የታተመበት የእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።
3. ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉት ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ባገኙበት መስከ ብቻ ነው
4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 500(አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ ክፍልና ቢሮ ቁጥር 28 መውሰድ ይችላሉ።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ሎት፤ 1 ብር 25,000.00 ፤ሎት 2፤ ብር 15,000.00 ፤ ሎት 3፤ ብር 5000.00 ፤ ሎት 4፤ብር 5000.00 ሎት ፤5 ብር 20,000.00 ፤ሎት 6፤ ብር 15,000.00 ፤ ሎት ፤7 ብር 8000.00 ፤ሎት 8 ፤ ብር 40,000.00 ፤ሎት 9 ፤ ብር 5,000.00 ፤ሎት 10 ፤ ብር25,000.00 ፤ ሎት 11፤ ብር 5000.00 በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ።
6. ተጫራቾች ያሸንፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስረከቢያ 10 ፐርሰንት በባንክ ወይም ለተቋሙ ካሸር በህጋዊ በማስያዝ ማቅረብ
7. ተጫራቾች በእያአንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ በመፃፍ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ሂሳብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 ማስገባት።
8. የእቃውን ዋጋ ሲሞሉ ት/ቤቱ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት። ሰነዱ ላይ የስራ አስኪያጁ ፊርማ እና ማህተም ማረፍ አለበት።
9. ተጫራቾች ተወዳዳሪዎች ባሸነፉበት እቃ ላይ ከናሙናው ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን ቀይረው የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ት/ቤት ቅጥር ቅቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 25 ይሆናል። ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት በማስገባት ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ት/ቤት ቅጥር ቅቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 25 (ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ) በዚሁ እለት ይከፈታል።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ኮተቤ መሳለሚያ አለፍ ብሎ ዋርካ ትምህርት ቤት አጠገብ ካራአሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 667 8641/011 667 8117/011-601 037
የካራአሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት