በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለራሱና በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች የተለያዩ የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለራሱና በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች የተለያዩ የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 15, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-/ክ/ከ//ፐ/ሰ/የሰ/ል/አስ/ፋ/ፐ/የመ/ግ/አስ/01/2018/19

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለራሱና በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ
  • ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 4 የጥገና ዕቃዎች
  • ሎት 5. የህትመት አገልግሎቶች
  • ሎት 6 የፎቶ ኮፒና ፕሪንት ቀለም
  • ሎት 7 የመኪና ኪራይ
  • ሎት 8. የአይቲ ዕቃዎች
  • ሎት 9 ድንኳን ኪራይ
  • ሎት10 የመኪና ጎማ
  • ሎት 11. የመኪና ልዩ ልዩ ማስዋብ
  • ሎት 12 የቀላል መኪና ጥገና

ሆነም በጨረታው ተሳትፋችሁ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራ

  1. ተጫራች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፤ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ፣ በወቅቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤ የምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጎቢነት የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ የመለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ሰነድ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ መክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ጽ/ቤት የክፍያ ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነድ ከገዙ በኋላ እዛው 6ኛ ፎቅ ከመንግስት ግዥ አሰተዳደር ቡድን ክፍል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
    • ተጫራቾች ለጨረታ የሚወዳደሩበትን እያንዳንዱ ሎት ወይም የበጀት ርዕስ በሲፒኦ ብር
    • ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች ( 5,000.00 ብር)
    •  ሎት 2 የደንብ ልብስ (5,000.00 ብር)
    • ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች (5,000.00 ብር)
    • ሎት 4 የጥገና ዕቃዎች (5,000.00 ብር)
    • ሎት 5 የህትመት አገልግሎቶች (10,000.00 ብር)
    • ሎት 6  የሮቶ ኮቴና ጥሪነት ቀለም (10,000.00 ብር)
    • ሎት 7 የመኪና ኪራይ (15,000.00 ብር)
    • ሎት 8 የአይቲ ዕቃዎች (15,000.00 ብር)
    • ሎት 9 የድንኳን ኪራይ (5,000.00 ብር)
    • ሎት 10 የመኪና ጎማ (40,00.00 ብር)
    • ሎት 11 የመኪና ልዩ ልዩ ማስዋብ (5,000.00 ብር)
    • ሎት 12 የቀላል መኪና ጥገና (35,000.00 ብር)
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥርና የዕቃውን ዓይነት በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመጻፍና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውሰጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ጽ/ቤት የመንግስት የግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ10ኛው ቀን 1100 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣዩ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
    • የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙናው ለማይቀርብባቸው የዕቃ ዓይነቶች በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የአገልግሎት ስራዎችን በተመለከተ ከድርጅቱ ጋር በመሄድ የሚታይ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ጥሬ ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ ድምር ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAፐ ጨምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል።
  7. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ መ/ቤቱ ባስቀመጠው ስፔስፍኬሽን መሰረት መሆናቸውን ወይም በሚቀርበው ናሙና፣ ጥራት፣ ዋስትና፣ አነስተኛ ዋጋ አጠቃሎ ለሚያቀርብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።
  8. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

አድራሻ፡- በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አራዳ ክፍል ከተማ በፐ/ሰ/የሰ/ል/ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል

የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ /ብርሃንና ላም ንግድ ባንክ ፊት ለፊት ነው፡፡

ስልክ ቁጥር-011-12-65-3-24

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በፐ/ሰ/የሰ/ል ጽ/ቤት/አስ/ፋ/ፑል የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን