Addis Zemen (Sep 15, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮ/ቀ/ክ/ከ/የወ/6/ጤ/ ጣቢያ በጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓም የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎችን፤ የጥገና ስራዎች የህትመት ስራዎችን፤ የጉልበት እና የጭነት አገልግሎቶችን እና የመሳሰሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለእያንዳንዱ ሎት መያዝ ያለበት የጨረታ ማስከበሪያ ብር
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ (37000.00) ብር
- ሎት 2 ደንብ ልብስ (37500.00) ብር
- ሎት 3 የጽዳት እቃዎች (30000.00) ብር
- ሎት 4 ቋሚ እቃዎች (45000.00) ብር
- ሎት 5 ህትመት ሥራዎች (30000.00) ብር
- ሎት 6 የጥገና እቃዎች (20000.00) ብር
- ሎት 7 የጥገና ሥራዎች (20000) ብር
- ሎት 8 የጭነት አገልግሎት ግዢ (10000.00) ብር
- ሎት 9 የጉልበት አገልግሎት ግዢ (10000.00) ብር
- ሎት 10 የመኪና መለዋወጫና ታፒሴሪ (20000) ብር
1. በመንግስት እቃ አቅራቢነት ከመንግስት ግዢ ኤጀንሲ የምስክር ወረቀት ያለው።
2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ግብር ከፋይ ቲን የምዝገባ ወረቀት ያላቸው ሆነው በዋጋ ዝርዝር ላይ ቫትን አካተው መሙላት አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየሎቱ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከቢሮ ቁጥር 47 መግዛት ይችላሉ።
5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ለማቅረብ የማይመቹ እቃዎችን በፎቶ እና በካታሎግ ማቅረብ ወይም መስሪያ ቤቱ ድርጅቱ ድረስ ለሚልካቸው ኮሚቴዎች ተፈላጊ እቃዎችን ማሳየት ይኖርባቸዋል።
6. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መሙላት አይቻልም።
7. ገዢው የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ድረስ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ እና ከላይ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በማስያዝ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለሳል።
10. አሸናፊዎች በሰነዱ ውስጥ በተገለጸው ጊዜ ገደብ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ያሸነፉበትን 10% ሲፒኦ በማሰራት ውል መዋዋል አለባቸው።
11. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ላይ በተቋሙ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
12. ተጫራቾች የሚያቀርቡአቸው እቃዎች የአገልግሎት ጊዜአቸው የሚያበቃበት ቀን ቢያንስ ከአንድ አመት በላይ መሆን ይኖርበታል።
13. የእያንዳንዱ ሎት ኦርጂናል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ መታሸግ ይኖርበታል።
14. መስሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. እስቶር እስከማስገባት ድረስ ያለውን የማጓጓዣና የጉልበት ወጪ ተጫራቹ ይሸፍናል።
16. የጨረታ ማስከበሪያው በትክክል የተቋማችንን አድራሻ መግለጽ ይኖርበታል።
17. ከስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የሚጻፉ ደብዳቤዎች በትክክል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ደብዳቤ መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል። እንዲሁም ደብዳቤዎቹ በጽ/ቤቱ ሃላፊ ፊርማ እና ቲተር መውጣት ይኖርበታል በተጨማሪም የተቋማችንን ሙሉ አድራሻ በትክክል መግለጽ ይኖርበታል።
18. በሚጫረቱበት እቃ ላይ እሴት ለሚጨምሩ ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ልዩ ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል።
19. የጨረታው የስራ ቋንቋ የፌዴራሉ የስራ ቋንቋ (አማርኛ) መሆን አለበት።
20. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡– ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ቤተል ከአደባባዩ ዝቅ ብሎ ክፍለ ከተማው አጠገብ ወይም ፖስታ ቤት ፊትለፊት።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 011 833 6993
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ጤና ጣቢያ