Reporter (Sep 20, 2026)
በድጋሚ የወጣ ያገለገለ መኪና ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲሴቢሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሲዬሽን /ኢ.ሲ.ዲ.ዲ/ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ለመመዝገብና ለማስተዳደር በወጣው አዋጅ መሰረት እ. ኤ. አ. በታህሳስ 2005 በምዝገባ ቁጥር 0321 በኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበርነት ተመዝግቦ ሲንቀሳቀስ የቆየና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ዳግም ለመመዝገብ በወጣው አዋጅ ቁ. 1113/2011 መሰረት ዳግም ተመዝግቦ በሀገራችን ሁሉን ያካተተ የማህበረሰብ እድገት ለማምጣት አካል ጉዳተኞች የጤና እና የትምህርት አገልግሎት፣ የስልጠና እና የሥራ ቅጥር እድል እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድሎችን ከአካል ጉዳት አልባ ወገኖቹ እኩል ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሁም አካል ጉዳተኞችንና ጉዳዮቻቸውን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በማህበራዊና ልማታዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንዲካተቱ አበክሮ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው።
ድርጅታችን ኢሲዲዲ በአሁኑ ሰዓት ኣገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን የ2010 ሞዴል ቶዮታ ባለሁለት ጋቢና ፒክ አፕ /Toyota Double Gabin Pick Up/ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከድርጅቱ ቢሮ መውሰድ የሚቻል ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት።
1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት (ከመስከረም 11 እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም.) በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3:00 – 11:00 ሰዓት) ከድርጅታችን ዋና መ/ቤት በአካል ቀርቦ ለጨረታ የቀረበውን መኪና መመልከትና የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። የቢሮአችን አድራሻ፡ ቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 4 የቤት ቁጥር 213 ደብረዘይት መንገድ በተለምዶ በቅሎቤት አካባቢ ከኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የአዲሰ አበባ መካከለኛ ታክስ ከፋዮች ቢሮ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የአማራ ባንክ የሚገኙበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ነው።
2. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት መኪና የሚያቀርቡትን ዋጋ በጨረታው ሰነድ ውስጥ በተዘጋጅው ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ጽ/ቤት አድራሻ በአካል በመገኘት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የመኪና ጨረታ ማስገቢያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ በድርጅቱ ስም (ኢትዮጲያን ሴንተር ፎር ዲስኤቢሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት/ Ethiopian Center for Disability and Development) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም ማለትም መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም ተዘግቶ በቀጣዩ የስራ ቀን ማለትም መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ሲሆን፣ አሸናፊው ወዲያው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ከፍለው ተሽከርካሪውን የመረከብ ግዴታ አለባቸው። በጨረታው አሸንፈው ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ ያስያዙት ገንዘብ/ ቢድ ቦንድ/ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል። የጨረታው አሸናፊ ስም ማዞሪያና ሌሎች ማንኛውም ተያያዥ ወጪዎችን ይሸፍናል።
5. በጨረታው ለሚሸነፉት ያስያዙትን የጨረታ ዋስትና ማስረከቢያ/ቢድ ቦንድ/ በጨረታው አሸናፊ ሙሉ ክፍያው እንደተፈፀመ ተመላሽ የሚደረግላቸው ይሆናል።
6. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 4 የቤት ቁጥር 213 ደብረዘይት መንገድ በተለምዶ በቅሎ ቤት አካባቢ ከኢትዮጵያ ገቢዎች ባለስልጣን የመካከለኛ ታክስ ከፋዮች ቢሮ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የአማራ ባንክ የሚገኙበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡ በመስመር ስልክ ቁጥር 011 416 8884 የሞባይል ቁጥር 251 90 457 0000 ወይም ኢሜይል።
Tenderecdd@ecdd-ethiopia.org ያግኙን።
ኢሲዲዲ ዋናው ቢሮ የኃላፊነት መተው መገስጫ/Disclaimer:
ኢ.ሲ.ዲ.ዲ. ሁሉንም ለአደጋ የተጋለጡ ህጻናትንና አዋቂዎችን ለመጠበቅ ቁርጠኛ የሆነ በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ የሚሰራ ድርጅት ነው። ኢ.ሲ.ዲ.ዲ. ለአደጋ የተጋለጡ አካል ጉዳተኞችን፤ ለአደጋ የተጋለጡ ህጻናትንና አዋቂዎችን ጨምሮ በልማትና በሰብአዊነት ፕሮግራሞች የሚተገብሩ ሰራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ አማካሪዎች ወይም ተቋራጮች የሚፈፅሙትን የወሲብ ብዝበዛ፣ በደል ወይም ትንኮሳን እንዲሁም ሙስናን ጨምሮ ለሚፈፀሙት ድርጊቶች ዜሮ ቶሌራንስ ፖሊሲም ያለው ድርጅት ነው። ስለዚህ፣ ከኢ.ሲ.ዲ.ዲ. ጋር የሚሰራ ማንኛውም ሰው /ድርጅት/ ለአደጋ የተጋለጡ ህጻናትንና ጎልማሶችን የጥበቃ ፖሊሲ፣ የወሲብ ብዝበዛና የጥቃት ፖሊሲን እና ሌሎች የህግ ማዕቀፎችን እንዲያከብር ይጠብቃል። የእነዚህ የተገለጹ ፖሊሲዎች እና ተዛማጅ ህጎች ጥሰቶች እስከ የስራ ውሉ መቋረጥ ድረስ የማስተካከያ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።