Addis Zemen (Sep 20, 2026)
የመጀመሪያ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡– ኢፕድ 005/2019
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ የእቃ እና የአገልግሎት ግዥ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡–
- ሎት 1. የመኪና ሰርቪስ እቃዎች
- ሎት 2. የጅግጅጋ ከተማ የህትመት ስርጭት የመኪና ኪራይ ለአንድ አመት በውል የሚሰራ
- ሎት 3. የሲዳማ ክልል ህትመት እና የሞተር ሳይክል ኪራይ ለአንድ አመት በውል የሚሰራ
- ሎት 4. ልዩ ልዩ የመስተንግዶ ማቅረቢያ እቃዎች
ስለሆነም፦ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልከቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርኻር ዋጋ ከቨት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር
- ለሎት 1 ብር 45,000.00
- ለሎት 2 ብር 40,000.00
- ለሎት 3 ብር 70,000.00
- ለሎት 4.ብር 25,000.00
በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸው።
4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምርያ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመከፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 1 56 98 69
ኢሜይል procurement@press.et
አድራሻ ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም መተሚያ ድርጅት ፊትለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት