ዳሸን ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ ከ900 በላይ ለሚሆኑ የባንኩ የቀጠና ፅ/ቤቶች እና ቅርንጫፍ ባንኮች የጽዳት፣ የመልዕክተኛ እና ሻይና ቡና ጥቅል አገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዳሸን ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ ከ900 በላይ ለሚሆኑ የባንኩ የቀጠና ፅ/ቤቶች እና ቅርንጫፍ ባንኮች የጽዳት፣ የመልዕክተኛ እና ሻይና ቡና ጥቅል አገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


Reporter (Sep 20, 2026), Fortune (Sep 20, 2026)

 በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ የማስታወቂያ ጥሪ

የጨረታ ቁጥር፡ DBOT03426/27

ዳሸን ባንክ . በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ 900 በላይ ለሚሆኑ የባንኩ የቀጠና /ቤቶች እና ቅርንጫፍ ባንኮች የጽዳት፣ የመልዕክተኛ እና ሻይና ቡና ጥቅል አገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል::

1. መግቢያ፣

ይህ የጨረታ ሰነድ በዳሸን ባንክ አክሲዮን ማህበር የጽዳት፣ የመልዕክተኛ እና ሻይና ቡና ጥቅል የሥራ አገልግሎት አቅራቢዎችን ጥሪ ለማድረግ የተዘጋጀ ሰነድ ነው:: የዚህ ጨረታ ዓላማም በዘርፉ በቂ የሥራ ልምድና አደረጃጀት ያላቸውን ህጋዊ ድርጅቶች በመምረጥ ባንኩ በሚሰጠው የሥራ ጥራት ደረጃ (Service level Standard) መሰረት በተገቢው መንገድ የፅዳትየመልዕክት እና የሻይ ቡና ሥራ ለማሰራት ማስቻል ነው።

2. የፅዳት፤ መልዕክት እና ሻይና ቡና ማስተንግዶ አገልግሎት ገዥ ዓላማ፤

ሙያዊ ብቃት ባለቸው ሰራተኞች እና ደረጃቸውን የጠበቁ የፅዳት ዕቃዎችን በመጠቀም የባንኩን ቢሮ እና አካባቢ ፅዱ እና ውብ ለስራ አመቺ ሁኔታ በመፍጠር እንዲሁም የመልዕከት እና ሻይና ቡና አገልግሎት በማቅረብ የባንኩን ሰራተኞችና ደንበኞች በማርካት የባንኩ ሰራተኞች በሞና ስራቸው ላይ ትኩረት በማድረግ በስራቸው አመርቂና ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ነው::

3. የአገልገሎቱ ይዘት፤

3.1 አገልግሎት ሰጪ የባንኩን ቢሮዎች፣ ቅርንጫፎች፣ መጋዘኖች ወይም ባንኩ የሚጠቀምባቸው ሌሎች ቦታዎች ከባንኩ በተሰጠው የሥራ መመሪያ መሠረት የሰው ኃይል እና ማቴሪያል በማቅረብ አገልግሎት መስጠት፣

3.2 ባንኩ እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ አገልግሎት አቅራቢዎች በቀጠና ወይም በቅርንጫፍ በማከፋፈል ውል ሊሰጥ ይችላል፣

3.3 ባንኩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

4. ተፈላጊ የሰነድ ማስረጃዎች፣

4.1 ድርጅቱ በዘርፉ በቂ ልምድ ያለውና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

4.2 የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የወቅቱን ግብር የከፈሉ፣

4.3 አገልግሎቱን ለመስጠት ያሰበበበት የሀገሪቱ አካባቢ በዘርፉ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ፈቀድ ያገኘ እና የታደሰ ያለው፣

4.4 ከባንኮች ጋር ወይም ትላልቅ ድርጅቶች ጋር በመስራት ልምድ ያለው

4.5 ከዚህ በፊት ከሰራበት ድርጅት የመልካም የስራ አፈፃጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

4.6 ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ክልሎች ለመስራት አቅምና ፍላጎት ያለው

4.7 የባንኩ ቅርንጫፎች ባሉበት ከተሞች ቢሮ እና ተወካይ ሰራተኛ ያለው

4.8 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር) የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፣

5. ተፈላጊ የሰውና የማቴርያል ግብአቶች፣

5.1 ደረጃቸውን የጠበቁ የፅዳት ማቴሪያሎችን በማቅረብ እና በመጠቀም ባንኩ በሚሰጠው የሥራ ጥራት ደረጃ (Service level Standard) መሰረት በተገቢው መንገድ የፅዳት የመልዕክተኛ እና የሻይ ቡና አገልግሎት ሥራ መስራት የሚችል ብቁ ሰራተኞችን የሚያቀርብ፤

5.2 ለቁጥጥር እና አስፈላጊ ግብአቶችን ለማቅረብ የሚውሉ መኪናዎች ያሉት፣

5.3 በባንኩ የሰው ኃብት ምደባ እቅድ መሰረት አስፈላጊውን የሰው ኃይል ለማሰማራት የሚችል፤

5.4 ብቁ ሰራተኞችን በማሰልጠንም ይሁን ለስራው ቅጥር መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰራተኞችን በመመደብ ማሰማራት የሚችል::

6 አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜ፤

ባንኩ አገልግሎቱን ለሁለት ዓመት የሚያሰራ ሲሆን እንደ ድርጅቱ የስራ አፈፃፀም ምዘና እና እንደ ባንኩ እና አገልገሎት ሰጪ ስምምነት የአገልግሎት ጊዜውን በተጨማሪም ለአንድ ዓመት ሊያራዝም ይችላል::

7. የጨረታ መሸጫ ማስገቢያና መክፈቻ ቀን

7.1 የጨረታ ሰነድ መሸጫ ድረገጽ | https://bids.extstewers.com/bifs-shop/dashen-bank-sc/ ወይም https://dashen.arotender.com/or afrotender.com ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከመስከረም 11 ቀን 2019 እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 / ድረስ ይሆናል:: የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሥራ ቀናት ከጧት 200 እስከ 600 ከሰዓት ደግሞ 700 እስከ 1100 ከታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመምጣት ወይም ከላይ በተገለጸው ድረገጽ ላይ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በመከፈል መግዛትና ማውረድ ይችላሉ::

7.2 በአካል ሰነድ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በዳሽን ባንክ አካውንት 180020002 በየትኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ አስገብተው ስሊፕ (slip) ወይም ማረጋገጫ የጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ማቅርብ ይኖርባቸዋል::

7.3 ጨረታው የሚዘጋው መስከረም 20 ቀን 2019 / ከቀኑ 1100 ሰዓት ሲሆን መክፈቻ ቀን በጊዜያዊነት ደግሞ መስከረም 21 ቀን 2019 / ከቀኑ 800 ከታች በተገለፀው አድራሻ ይሆናል::

7.4 ባንኩ የተሻለ ነገር ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ዳሽን ባንክ ዋናው /ቤት

ብሔራዊ ባንክ ፊት ለፊት

ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት መምሪያ

ቢሮ ቁጥር 7 ወለል

ስልክ 0115180356 የውስጥ ቁጥር 4171/3153

ዳሽን ባንክ ሁልጊዜ አንድ እርምጃ ቀዳሚ!


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *