ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣ የአይቲ ዕቃዎች፣ የጽዳት ማሽነሪዎች፣ የማሸጊያ ፕላስቲክ መጠረዣ ሪንግ ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣ የአይቲ ዕቃዎች፣ የጽዳት ማሽነሪዎች፣ የማሸጊያ ፕላስቲክ መጠረዣ ሪንግ ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ (በድጋሚ የወጣ)

CN/DE/06/19

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በድርጅታችን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣ የአይቲ ዕቃዎች፣ የጽዳት ማሽነሪዎች፣ የማሸጊያ ፕላስቲክ መጠረዣ ሪንግ ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 300.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል። ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሁኔታ ቀጠሮ በማስያዝ ገርጂ በሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት፣ ቃሊቲ በሚገኘው ጃቲ የዕቃ ግምጃ እንዲሁም አማልጋ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ግምጃ ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መሰከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ከጨረታ ዋጋቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋርንቲ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው

የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-156 99 92

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *